በኢትዮጵያ የብራንድ አምባሳደርነት ታሪክ ከፍተኛው ክፍያ ለአርቲስት አብርሀም ወልዴ ተከፈለው።

አምጊፍት ሪልእስቴት አርቲስት አብርሀም ወልዴን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።

አርቲስት አብርሀም ወልዴ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ የሚያገለግልበትን ስምምነት በዛሬው እለት ፈጽሟል።

ላለፉት ሁለት ሶስት አስርት አመታት በቤት ግንባታ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝው ጊፍት ሪልእስቴት ባሁኑ ሰአት ከፍተኛ የቤት ግንባታ እና ሽያጭ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ስምምነቱ በየሶስት አመቱ የሚታደስ ይሆናል ተብሏል።

አርቲስት አብርሀም ወልዴ በመመረጡ ደስ መሰኘቱን ገልጾ እኔም መርጬ ነው አምባሳደር የሆንኩት ብሏል።

ይህንን ስራው በተደራጀ መንገድ እና ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው የአለም ሀገራት የጊፍት ቤቶችን እንዲያስተዋውቅ ነው አብርሀም ወልዴ ብራንድ አድርጎ የተመረጠው ተብሏል።

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ ጊፍት ሪል ስቴት በላቀ ጥራት ቤቶቻችን ለመገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን በስምምነቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply