በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ የቡድን 7 ሃገራት ልዑካን የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት የአተገባበር ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጡ ።ሃገራቱ የአፍሪቃ ኅብረት አዲስ አ…

በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ የቡድን 7 ሃገራት ልዑካን የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት የአተገባበር ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጡ ።

ሃገራቱ የአፍሪቃ ኅብረት አዲስ አበባ ውስጥ ያሰናዳው የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ግምገማ መጠናቀቅን ተከትሎ ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ፦ የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የአውሮጳ ኅብረት እና የቡድን 7 ሃገራት ልዑካን በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ማስፈን  አስፈላጊነትንም አስምረውበታል ። 

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለመበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ ለማዋሃድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጠዋል ።

የቡድን 7 የበለፀጉ ሃገራት ልዑካኑ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል ።

ስለ ውይይቱ ውጤት ከፌዴራል መንግሥት ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ።

ሕወሓት በበኩሉ ጉዳዮን አስመልክቶ ትናንት መግለጫ አውጥቷል ።

በመግለጫውም፦ በሕወሓት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል ያሉ የተራራቁ አቋሞችን ለማቀራረብ፣ ፖለቲካዊ ውይይትን ጨምሮ ቀጣይ መድረኮችን ለማካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱን ዐስታውቋል ።

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply