በኢትዮጵያ የአይን ብሌን ጠባሳ ሀኪሞች ቁጥር 12 ብቻ ነው ተባለ፡፡የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በመላው ሀገሪቱ የአይን ብሌን ለጋሾችን የሚረከቡ እንዲሁም የአይን…

በኢትዮጵያ የአይን ብሌን ጠባሳ ሀኪሞች ቁጥር 12 ብቻ ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በመላው ሀገሪቱ የአይን ብሌን ለጋሾችን የሚረከቡ እንዲሁም የአይን ብሌን ጠባሳ ዶክተሮች ቁጥር 12 ብቻ ነው ብሏል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ታዬ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 203 የአይን ብሌን ከለጋሾች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል 288 ሰዎች አይናቸውን ለመለገስ ቃል እንደገቡ የገለፁት ሀላፊው ነገር ግን ካቀድነው ከግማሽ በታች ነው ብለዋል።

ያለን ባህል የአይን ለጋሾችን ቁጥር እንደቀነሰባቸው የሚያነሱት ሀላፊው በተለይም የተገቡ ቃሎች እንደማይተገበር አንስተዋል።

የአይን ብሌን በአጭር ጊዜ እንደሚሰራ እንዲሁም ሙሉ አይኑ ሳይሆን ከላይ ያለችው ልባስ ነው ምትነሳው የሚሉት ሀላፊው በዚህም አመለካከታችን ሊቀየር ይገባልም ብለዋል።

በ20 አመታት ውስጥ ወደ 3 ሺ ገደማ የአይን ንቅለ ተከላዎች እንደተደረጉም ሰምተናል።

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተጠና ጥናት ከ3 መቶ ሺ በላይ ሰዎች በአይን ብሌን ጠባሳ የአይን ብርሀናቸውን እንዳጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በለአለም አሰፋ

ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply