
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ ወረርሽኙ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሆነ። ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ መገኘቱ የተረጋገጠው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የነበረ ሲሆን እነሆ ከአንድ ዓመት ከአንድ ወር በኋላ የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ ማለፉ ታውቋል።
Source: Link to the Post