በኢትዮጵያ ያለውን የልማት መሬት የማግኘት ችግሮች ላይ ያተኩሩ የፖሊሲ ሰነድ ይፋ ተደረገ፡፡

የአውሮፓ ቻምበር ባለሀብቱ ከኢንድስትሪ ውጪ ያሉ መሬቶችን ለማግኘት የሚያጋጥሙ ውጣ ውረዶችን ያማከለ የጥናት ሰነድ ይፋ አድርጓል።

የጥናቱ ዋና አላማ የሀገር ውስጥ እና የወጭ ባለሀብቶች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች የሚዳስስ ሲሆን በመንግስት ሊታዩ የሚገቡ ግኝቶችና ምክረ ሀሳቦችን የያዘ ነው።

በተለይም ከኢንድስትሪ ውጪ ያሉ መሬቶችን ለባለሀብቱ ለመስጠት የነበረው ዉጣ ዉረድ ከባድ እንደሆነ ሲነሳ ባለሀብቱ መሬቱን ለማግኘት የሚያገኘውንም ጥረት ከባድ እንዳረገውም ተነስቷል፡፡

ከዚህ ቀደም መንግስት 1161 የሚባል የመሬት አዋጅ አውጥቶ 5 አመት እንዳለፈ ሲነሳ አፈፃፃሙ ላይ ግን የመሬትን ችግር የሚያቃልል ስራ እንዳልተሰራ ተነስቷል፡፡

በጥናቱ የተገኙት ግኙቶችም ባለሀብቱ መሬትን ለማግኘት ባለው ሂደት ውስጥ የቢሮክራሲ ችግሮች ግልፀኝነት እንዲሁም ፀጥታው ለኢንቨስተሩ መሬቱን እንዳያገኝ ምክንያት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በመጨረሻም የፖሊሲ ሰነዱ በኢትዮጵያ መንግስት ሊታሰብባቸውን ያለውን ነጠብ ያስቀመጠ ሲሆን ከነዛ ውስጥም ፍትሀዊነት ግልፅ የሆነ አሰራር እንዲሁም መዋቅራዊ መስተጓግሎች በደንብ ሊታዪ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply