በኢትዮጵያ ያለው የሰላም እጦት ወጣቶች ወደ ሱስ እንዲገቡ እያደረገ ነው ተባለበአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት አስራት ጫካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገ…

በኢትዮጵያ ያለው የሰላም እጦት ወጣቶች ወደ ሱስ እንዲገቡ እያደረገ ነው ተባለ

በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት አስራት ጫካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የሰላም እጦትና የስራ አጥነት ቁጥር መጨመር በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ለመጣው የሱስ ተጠቂዎች ቁጥር ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

የህክምና ባለሙያው በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሚሊዮኖች መፈናቀል እና ሞት ምክንያት ሲሆን፣ ቁጥራቸው የማይገመት ህጻናትንም ቤተሰብ አልባ አድርጓልም ብለዋል፡፡

ጦርነት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ መፈናቀልና ድርቅ ለሱስ አጋላጭነት ቀላል የማይባል ሚና እንደሚጫወቱ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ።

በኢትዮጵያ ከ 5.5 ሚሊየን በላይ ህጻናት ወላጅ አልባ እንደሆኑ የዩኒሴፍ ሪፖርት ያመላክታል ።

ይህም ህጻናቱን ለሱስ የሚኖራቸውን ተጋላጭነት ከፍ እንደሚያደርገው ታውቋል።

ለአለም አሰፋ

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply