በኢትዮጵያ ጀግኖች አምባ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ከ400 በላይ ሙሉ ልብስ ድጋፍ ተደገረ

በኢትዮጵያ ጀግኖች አምባ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ከ400 በላይ ሙሉ ልብስ ድጋፍ ተደገረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ጀግኖች አምባ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ከ400 በላይ ሙሉ ልብስ ድጋፍ ተደገረ፡፡
ድጋፉ በስዊዘርላንድ ሄልቤክስ በተባለ የበረራ ድርጅት ከምትስራ እና ለዓመታት በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርታ ከምትገኘው ኤሚ በቀለ የተደረገ ነው፡፡
በዚህ በፊትም ለጌርጌሴኖም የአዕምሮ ህሙማን መረጃ እና ለዶክተር ስሜነሽ የካንሰር ህሙማን መርጃ ማዕከል የአልባሳት እና ገንዘብ ድጋፍ አድርጋ ነበር፡፡
ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ ጀግኖች አምባ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች እና ለመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አድርጋለች፡፡
ድጋፍ ያደረገችውን አላባሳትንም ስዊዘርላንድ ከሚገኘው ኮርፐስ የተባለ ኩባንያ ድጋፍ እንዳደረገላት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ በነፃ አልባሳቱን ወደ ሃገር እንዲገባ ማድረጉን የገለፀችው ኤሚ ለዚህም ምስጋና አቀርባለች፡፡
በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትብብር “ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ባለፈው ህዳር ወር ላይ መቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡
ድርጅቱ የተቋቋመው በጦር ሜዳ ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት እንክብካቤ ለማድረግና የሕይወት መሥዋዕትነት የከፈሉ የሠራዊት አባላት ልጆችን ሰብስቦ ለማሳደግ ነው ፡፡
ይህም ቀድሞ በጀግኖች አምባ የነበሩትን የጦር ጉዳተኞችን የሚያጠቃልል መሆኑም ይታወቃል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በኢትዮጵያ ጀግኖች አምባ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ከ400 በላይ ሙሉ ልብስ ድጋፍ ተደገረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply