በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ለመፍታት በምክር ቤቱ የህግ ክፍል እየታየ ነው ተባለ፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በስሩ ስድስት ቋሚ ኮሚ…

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ለመፍታት በምክር ቤቱ የህግ ክፍል እየታየ ነው ተባለ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በስሩ ስድስት ቋሚ ኮሚቴዎች መኖሩንና ከእነዚህ አንዱ በሆነው የህግ ክፍል ጉዳዩ እየታየ መሆኑ የስራ አስፈፃሚው አባል የሆኑት አቶ ፈይሰል አብዱላዚዝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በፓርቲዎች መካከል አለመግባባት በሚፈጠር ወቅት ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋመው የህግ ክፍሉ ለችግሩ መፍትሄ እየፈለገ መሆኑን ነግረውናል፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈፃሚው በኩል በሀገሪቱ ያለው አሳሳቢ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ማውጣቱ የሚታውስ ነው፡፡
ይህን ተከትሎ እራሱን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዚያዊ የጋራ ምክር ቤት ብሎ የጠሩ ፓርቲዎች መርህ ይከበር በሚል የስራ አስፈፃሚውን መግለጫ ተቃውመው መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚው በአምስት ቀናት ውስጥ መግለጫ ይስጥ፣ያለበለዚያ የራሳችንን አዲስ የጋራ ምክር ቤት እናቋቁማለን ማለቱም ይታወሳል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ፈይሳል ጉዳዩን ወደ ህግ ክፍሉ በመውሰድ ውሳኔውን እየተጠባበቁ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

በጊዜያዊ ኮሚቴው የተጠቀሰው በርካታ ፓርቲዎች አብረዋቸው እንዳሉ የተነሳው የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ ከአምስት ፓርቲዎች እንደማይበልጡ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በጠቅላላ ጉባኤ ጀምሮ የአገው ሸንጎ ፓርቲ ተቃውሞ ያሰሙ የነበረ ሲሆን፣ በመግለጫውም ላይ የአገው ሸንጎን ጨምሮ ኦነግ እና ህዳሴ ፓርቲ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአገው ሸንጎ ፓርቲ አመራር የአገው ጉዳይ ለምን በመግለጫው አልተካተተም በሚል ግሩፕ በመፍጠር ለመገንጠል መሞከራቸውን ነው ለኢትዮ ኤፍ ኤም የገለፁት፡፡

በፖሊቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ስር ያለው የህግ ክፍል ምክር ቤቱ የፈጠረውን የዲሲፒሊን ግድፈት ተመልክቶ በቅርብ ምላሽ እንደሚሰጥ አቶ ፈይሰል ገልፀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply