በኢትዮጵያ 10 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ከኩላሊት ህመም ጋር በተያያዘ በስቃይ ላይ ይገኛሉ ተባለ፡፡5 መቶ ሺህ የኩላሊት እጥበት እንደሚያስፈልጋቸው የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክት ተ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ZaPu1UsMR7mfm4FvwPW8JUHddM_bn2rxk8pO-7beR7e-vm1TUemsV-Z1_OBuVB7aGB5VLx9Iqvb9dxsKyKafqMw5KtLFOt9cZzylUpkfn-W4UEK3uq-9Os1wXC6uuhkHb5EUSlbLpwAI4lwckrchwhRltAhLwgGfaqnn9pDonBTMttPXR5I7-Bws1e5clDwp1eDRGCEThsXIjNmf4UkuA3koEUxQvIPemy2gGCeilAiLW4ZDUZUCFQHuLHSnoDNhuhyQBqEHOvoP6NUcWbUEKZJrm8sj0TjIWz0CjG0dioBsmHepquSZeG_YG-oznVt1cRAkKKRzox-LZDmwLCURsA.jpg

በኢትዮጵያ 10 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ከኩላሊት ህመም ጋር በተያያዘ በስቃይ ላይ ይገኛሉ ተባለ፡፡

5 መቶ ሺህ የኩላሊት እጥበት እንደሚያስፈልጋቸው የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክት ተነግሯል።

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በሀገሪቱ ከ500 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት (የዲያሌሲስ) ያስፈልገዋል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል፡፡

ለመኖር የሚታገሉ እና ህይወታቸውን ለማቆየት የሚታሉ ታካዎች በቁጥር አነስተኛ ናቸው ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ፤በእየለቱ ምን ያህሉ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እያደረገ ለመሆን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም እንደ ምክንያት 4 ሺህ የሚሆኑት አገልግሎቱን የሚያገኙ ቢኖሩም በነገው እለት ህይወታቸው የሚያልፍ እና ንቅለ ተከላን የሚያከናውኑ በመኖራቸው ቁጥሩ ሊቀንስበት የሚችልበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቁሟል፡፡

ዜጎች ለኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ መጠን እና የጊዜ ቆይታ ሲነገራቸው አገልግሎቱን የሚያቋርጡ ዜጎች ድርጅቱ ጋር የማይደርስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በመሆኑም በገንዘብ እጦት ምክንያት የዲያሌሲስ ህክምና የሚያቋርጡ እና ለህልፈት የሚዳረጉ ዜጎች መኖራቸውንም ሰምተናል።

በሀገራችን 48 የሚሆኑ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ቢኖሩም፤ አሁንም አገልግሎቱ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የህክምና ክትትሉን እያቋረጡ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply