በኢትዮጵያ 1311 የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ።
በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ እንደተናገሩት ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።በዚህም 1,311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው መውጣታቸውንና ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ሕይወታቸው ማለፉንም አክለዋል።
በነገው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት መሆኑን ጠቁመዋል።

Leave a Reply