በኢትዮጵያ 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ይፈልጋሉ ተባለየወሽ ክላስተር አስተባባሪ ሎራ ኦንኬ 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች በአስቸኳይ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ እን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/mCAkhhdHxXf245T3zZ5Dq72fLjLIHwWylIWjFhSqZxfFBst3iCgDwekd1t9d-S8v0M3BG0Cin9IMG-PzatOA31Sa-4af08NOQ_NV3_29V_mjCs8J905WJI1km42NoU_EDhfUv8GSEi5ultruJYEg7EOntMdTVHSuHoW8fkLSPm3jrWGPBxef9rouWxltWP1B3fbPAh6ieRUQj5xc9FzjPv6M3N-4eLxyC850IdLlauvth1MWBWD94XurFDLYS-tGWmKoLwJKEoYNNVizwTzvez2Daz4IDDblABsR6Z8y_mFvjxAG7dykkgypkl-iXMyQjc_7Zud0uiQdj0nDt2WORA.jpg

በኢትዮጵያ 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ይፈልጋሉ ተባለ

የወሽ ክላስተር አስተባባሪ ሎራ ኦንኬ 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች በአስቸኳይ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተናግረዋል፡፡

ከ 15.2 ሚሊዮን ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ከሚያስፈልጋቸዉ ዜጎች መካከል ለ 8.8 ሚሊዮን ሰዎችን ለማዳረስ እየሰሩ መሆናቸዉን አንስተዋል ፡፡

አስተባባሪዋ 8.8 ሚሊዮኑን ህዝብ የዉሃ አቅርቦት ተደራሽ ለማድርግ 172 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ለጣቢያችን አስረድተዋል ፡፡

ተቋማቸዉ በተቀላጠፈ ምልኩ ስራዉን ሰርቶ ለማህበረሰቡ በፍጥነት ተደራሽ እንዳያደርግ በየሃገሪቱ በየቦታዉ ያለዉ የጸጥታ ሁኔታ ችግር ፈጥሯል ነዉ ያሉት፡፡

የኮሌራ በሽታ ወረርሺኝ ፤የአየሩ ሁኔታ ፤ለስራዉ የሚያስፈልጉት እያንዳዱ ግብኣቶች የዋጋ ንረት እንዲሁም የዜጎች አፈና ለስራቸዉ ችግር እንደፈጠረባቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ፡፡

ልዑል ወልዴ
ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply