በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ አደረጉት ባለዉ ዓመታዊ ጥናቱ ላይ እንደገለፀው በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑ የ 2ኛ እና የ 3ኛ ክፍል ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አረጋግጫለሁ ብሏል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሲያከናዉን የቆየዉን ጥናት ይፋ አድርጓል ። በዚህም ከትግራይ ክልል በስተቀር በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ 401 ትምህርት ቤቶች እና በ 16 ሺህ ተማሪዎች ላይ በተደረገ ጥናት ዉጤቱ መገኘቱን አስታዉቀዋል።

ይህ ቁጥር ከባለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር በመጠኑ መሻሻል አሳይታል የተባለ ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የተደረገው ጥናት ምንም ማንበብ የማይችሉት 63 በመቶዎች እንደነበሩ ጥናቱ አመላክቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 07 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply