በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ታጣቂዎች የከብት ዝርፊያ እየፈጸሙ እንደሚገኙ ተነገረ፡፡በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች የታጣቂዎች ትንኮሳ አሁን ላይ ቢቆምም የከብት ዝርፊያዎች አሁንም እንደሚ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/v9J8Kh_L_qZ6h1luoAxpe_gHyknpa3h4m_tdyQJBCrKsKWnwRUKeuV-MQ8gaFEBx4zPXwdkelfyvmHCMa6e6No4fGW8ZWiuC8nYWdbHuf9AQK6whjRpq9Qz_ESmH_7YBGU_DvoVtzlbFJ3F1XXT6_135ggl_hNmaP5Lgg8OxDmoD6p-dPhqpZZIRllX4X5mxbid2y3lzbdjmNvHsq63n0nbg0HMR6ekme31hYUiUkAqLIuGJvOQVdSA6X0O8eqas4-di8t2YF9unB2yYawXqx5AFHQuWHpWZ19CWUtMFJUJPWEwWLASi0BDTZwIPXQW7eHIyAIODfQliioJ9ONesOw.jpg

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ታጣቂዎች የከብት ዝርፊያ እየፈጸሙ እንደሚገኙ ተነገረ፡፡

በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች የታጣቂዎች ትንኮሳ አሁን ላይ ቢቆምም የከብት ዝርፊያዎች አሁንም እንደሚፈጸሙ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታዉቋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከዚህ ቀደም በድንበር አካባቢ የሱዳን ታጣቂዎች ያደርሱት የነበረዉን ጥቃትና ትንኮሳ አቁመዋል፡፡

በዞኑ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ የተርጋጋ መሆኑን የነገሩን ዋና አስተዳዳሪዉ፣ ይሁን እንጅ የከብት ዝርፊያ ወንጀሎች እንደሚሰተዋሉ አንስተዋል፡፡

ከእንሰሳት ስርቆትና ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ በሱዳንና ኢትዮጵያ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የሰላም መደፍረስ ለመፍታት በጋራ እየሰተሰራ እንደሆነም አቶ ቢክስ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢ ከእንስሳት ስርቆት ጋር በተያያዘ ግጭቶች ሲነሱ ቆይተዋል።

እነኝህን ችግሮች መፍታት የሚያስችልና ከሁለቱም ወገን የተሰረቁ እንስሳት ወደየአካባቢዎቹ እንዲመለሱ የሚያደርጉ ውይይቶች መካሄዳቸዉንም ሰምተናል፡፡

በሌላ በኩል የአካባቢዉ የፀጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ተከትሎ የግብርና ስራዉን ለማነቃቃት እየተሰራ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪዉ ለኢዮ ኤፍ ኤም አስታዉቀዋል፡፡

በቅርቡም በመቶ ሺህዎች ለሚሆኑ የቀን ሰራተኞች የስራ ዕድል በመፍጠር የእርሻ መሬት ዝግጅት ስራዎች ይከናወናሉ ተብሏል፡፡

በአባቱ መረቀ

መጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply