በኢትዮ-ጂቡቲ ዋና መስመር የህወሓት የሽብር ቡድንን አገር የማፍረስ እኩይ አላማ ለማሳካት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በኢትዮ-ጂቡቲ ዋና መስመር የህወሓት የሽብር ቡድንን አገር የማፍረስ እኩይ አላማ ለማሳካት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮ-ጂቡቲ ዋና መስመር የህወሓት የሽብር ቡድንን አገር የማፍረስ እኩይ አላማ ለማሳካት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን በሚሌ ጉምሩክና አካባቢው ለግዳጅ የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት አስታውቀዋል። ከአዲስ አበባ – አዋሽ – ሚሌ – ጋላፊ – ጂቡቲ የተዘረጋውና የአገራችን የወጭና ገቢ ንግድ ዋና ኮሪደር የሆነውን የአስፓልት መንገድ ተቆጣጥሬያለሁ በሚል የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መጠመዱ ተገልጧል። ይህ የህወሓት ሽብር ቡድን ሃሰተኛ መታወቂያዎችን በማስያዝና የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ለድብቅ አላማ ያሰማራቸው ተላላኪዎቹም ከተለያዩ የደንብ ልብሶችና ወታደራዊ መጠቀሚያዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች ተናግረዋል፡፡ በፍተሻ ጣቢያው ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከአፋር ክልል ልዩሃይልና ሚሊሻ ጋር በጥምረት በመሆን የተቀናጀና የተጠናከረ ፍተሻ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት የሰራዊቱ አመራሮች ናቸው። በቀጣይነትም በየትኛውም መልኩ የሽብርተኛው የማፍረስ ውጥን እውን እንዳይሆንና በዋናው መስመር የተለመደው የትራፊክ ፍሰት እንዲቀጥል ቀን ከሌሊት ተግተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡ በሚሌ ጉምሩክ ጣቢያ የሚሰሩ የፍተሻ ባለሙያዎችና በመስመሩ የሚመላለሱ የከባድና ቀላል መኪኖች አሽከርካሪዎች በበኩላቸው የሃሰት ወሬዎችን እየፈበረኩ አገር ለማፍረስ የሚታትሩ የጁንታው ቅልብ ልሳኖች የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች ወደ ጎን መተው እንደሚገባቸው መክረዋል። ይልቁንስ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ካሉ የፀጥታ ሃይሎች ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትር በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply