በኢትጵዮያ ከ60 አመታት በላይ ልማት ያልጎበኛቸው እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር ያልተዋወቁ አካባቢዎች መኖራቸው ተነገረ።ከአጼ ሐይለስላሴ ስርዐት መንግስት መውደቅ አንስቶ እስካሁኑ የመንግስት…

በኢትጵዮያ ከ60 አመታት በላይ ልማት ያልጎበኛቸው እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር ያልተዋወቁ አካባቢዎች መኖራቸው ተነገረ።

ከአጼ ሐይለስላሴ ስርዐት መንግስት መውደቅ አንስቶ እስካሁኑ የመንግስት ስርአት ድረስ ከልማት ጋር ያልተዋወቁ የክልል እና የዞን አካባቢዎች መኖራቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

ከዚህ በፊት ሀገሪቷን ያስተዳደሩት መንግስታት የረሷቸውና ትኩረት ያልሰጧቸው አካባቢዎች ዛሬም ድረስ ከመሰረተ ልማት ጋር ተራርቀው ይገኛሉ ብለዋል።

የፓርቲ አመራሮቹ ይህንን የተናገሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገሪቱ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎች አንሰተዋል።

አመራሮቹ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አመራሮች በሀገሪቱ እየተፈጸሙ ባሉ ዘርፈ ብዙ ጥቃቶች እና ግጭቶች እጃቸው እንዳለበት ሀገር ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ተስፋ የጣሉበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጅምሩ በብልጽግና ፓርቲ ሰዎች የበላይነት መያዙን የተናገሩት ፓርቱዎቹ የታማኝነት እና የአካታችነት ጥያቄው መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባው ተናግረዋል።

በውይይቱ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትግራይ ህዝብ ችግሮቹ እና ጥያቄዎቹ በተወካዮቹ በኩል ማቅረብ የሚችልበት ሁኔታ የሚል ይገኝበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርቲ አመራሮች ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡም ሲሆን ፓርቲዎች የውስጥ ችግራቸውን ሁሌ መንግስት ላይ መጣላቸው ትክክል አይደለም ብለዋል።

መንግስት ሀገር ውስጥ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅሙ በፈቀደ መጠን ለመርዳት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።  

በዚህ ውይይት ላይ ከ400 በላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች መሳተፋቸው ተገልጿል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

Source: Link to the Post

Leave a Reply