በኢንደስትሪ ፓርኮች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በኢንደስትሪ ፓርኮች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች መሰረታዊ የመብት ጥሰቶች…

በኢንደስትሪ ፓርኮች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኢንደስትሪ ፓርኮች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች መሰረታዊ የመብት ጥሰቶች መቀጠላቸዉ እንዳሳሰበዉም ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡
በግጭቱ ምክንያት ተፈናቅለዉ በሚገኙ ሕጻናትና ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽኑ ባወጣዉ ሪፖርት አመላክቷል፡፡

የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት ሳቢያ በሴቶችና ሕፃናት መሰረታዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውም ታዉቋል፡፡
በሀገሪቱ በተከሰቱ የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት ምክንያት የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ህፃናትና ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳታቸዉ ተነስቷል፡፡
በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለጾታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጋላጭ መሆናቸውንም ኮሚሽኑ በመግለጫዉ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ልዩ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረጉ የሰብአዊ ድጋፎች አለማግኘታቸው ተደራራቢ የመብቶች ጥሰትን አስከትሏል ነዉ ያለዉ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመስከረም 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 36 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
በኢትዮጵያ በተከሰቱት ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት ሕፃናት ከመንግሥት፣ ከማኅበረሰቡ እና ከቤተሰብ ማግኘት ያለባቸው ጥበቃ በመጓደሉ ለተደራራቢ የመብቶች ጥሰት መዳረጋችን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በብሔራዊ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥም ለሕፃናትና ለሴቶች ሰብአዊ መብቶች በቂ የሕግ ከለላ በመስጠት ረገድ ክፍተቶች መስተዋላቸውም ተጠቅሷል።
በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል በተነሳው ጦርነት በሴቶች እና በሕፃናት ላይ ስልታዊ በሆነ መልኩ ጭምር ጥቃት እንደተፈጸመባቸዉ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ለተፈጸሙ ጥቃቶች ውጤታማ ፍትሕ እና መፍትሔ እንዳላገኙም ኮሚሽኑ በሪፖርቱ አንስቷል፡፡
በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች በተለያየ ወቅት በተነሱ ግጭቶችም ሴቶችና ሕፃናት ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መጋለጣቸው ተጠቅሷል።

በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply