በኢንዱስትሪ ፓርኮችና አዲስ በሚከፈቱ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የተለያዩ በደል እና ጥቃቶች ይደርሰባቸዋል ተባለ፡፡የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በማኅበር…

በኢንዱስትሪ ፓርኮችና አዲስ በሚከፈቱ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የተለያዩ በደል እና ጥቃቶች ይደርሰባቸዋል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በማኅበር ለመደራጀት የሚፈልጉ ሠራተኞች በአንድ አንድ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፍቃድ ማግኘት አልቻሉም መባሉን ሰምተናል፡፡

ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው በኢሠማኮ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ማህበራት ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ አቶ ድሪብሳ ለገሰ እንደሚሉት ከሆነ በአደማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሳሰሉት ፓርኮች ሰራተኞች በብዙ ጥረት እንዲደራጁ ቢደረግም አሁንም በደሎች እንደቀጠሉ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በመሳሉት ፓርኮችም ከ130 በላይ ድርጅቶች ያሉ ቢሆንም የሰራተኛውን በማህበር የመደራጀትና ለችግሩ አቤቱታ የሚያቀርብበት ተቋም እንዳይኖር መከልከለቸውን ነግረውናል፡፡

በሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 31 ላይ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማኅበር የመደራጀት መብት አለው ሲል ይደነግጋል፡፡

ይሁን እንጂ የሠራተኛ ማኅበራት ጩኸት ሰሚ በማጣቱም በርካታ ሠራተኞች፣ የመደራጀት መብታቸው ተነፍጎና የሥራ ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቆ ኑሮአቸውን ለመግፋት ተገደዋል፡፡

በአዲስ አበባ፣ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርከች እና አዲስ በሚከፈቱ ፋብሪካዎች ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፃታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ መድረሳቸውን ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባሰጠናው ጥናት ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡

የስብስቡ ዋና ዳይሬክተር መሠረት አሊ ከጣብያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሠራተኛው የሚደርስበትን በደል የሚያሰማበት ማህበር ባለመኖሩ ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላሉ፡፡

የአሠማኮ እንዲሁም ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደገለፁን ከሆነ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣በኢስተርን ኢዱስትሪ ዞን እንዲሁም በአማራ፣ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ክልሎችና ከተሞች የሠራተኛ ሰብዓዊ መብቶች አሳሳቢ መሆኑን ነግረውናል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽንን ብንጠይቅም በማስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ምንም ዓይነት የሰራተኛ በደሎች ፃታዊ ጥቃቶች የሉም ሲል ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጶያ በቅርቡ ባስጠናው ጥናት መሠረትም በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣አዲስ በሚከፈቱ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ውስጥ በሚሰሩ ሴት ሰራተኞች ላይ ፃታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እንደሚደርሱ መግለፁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply