
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቫይረስ መከሰቱን የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ድረስም ስምንት ያህል ዜጎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸው ነው የተነገረው፡፡
የኢቦላ ቫይረስ መነሻ እንደሆነች የሚነገርላት ኢኳቶሪያል ጊኒ አሁን በዚህ ማርበርግ በተሰኝ አዲስ ቫይረስ እየተፈተነች ትገኛለች ተብሏል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት እጅግ ፈጣን እና ገዳይ የሆነ ቫይረስ ሲል ገልጾታል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ሃገሪቷ ቫይረሱ በተከሰተባት ኪኔተም በተሰኝችው ግዛት ላይ የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲገታ ውሳኔ አሳልፋለች፡፡
እየወጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 200 ያህል ዜጎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ማርበርግ የተሰኘው ይህ ቫይረስ ከኢቦላ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይነት ያለው ተላላፊ በሽታ መሆኑንም የአለም የጤና ድርጅትን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 08 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post