በኤሌክትሪክ እና በአነስተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚሰሩ 25 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ላቀርብ ነው አለ አቤት ትራንስፖርት በሚቀጥሉት 5 አመታት 25 ሺህ በኤሌክትሪክ እና አነስተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚሰ…

https://cdn4.telesco.pe/file/FSCkbESkbM7OFGmBwFgs3OjNWYn-7ZBfWISMxOU67S7lzWGVFGuj5GfJ_TQhOyFdjdH00dU2fAqCVLTlalg6sP7EELzVoHa9Qw3LbNjKg1Ca5bgz8LRt27pxo97LAZgZGPUe4RBfZP91quq9NXbwpcNZ-OU_7Pz7DG6VTIVB47_SpFRvZX7JfCzFGCyqH44-CP-Q4dFx_8sZyisSGza7QNkV4sbbA7O8JAsd1NpNvPu_HFTadcGil8J34_7pGvDiBBsuXkfCZcK1apseTEu5KjxN3aa4x1zBAtfU7CmpKNb48gS3lWZ0a1djw-otOXa2agBq71QlBsyV0bgZP2jtfQ.jpg

በኤሌክትሪክ እና በአነስተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚሰሩ 25 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ላቀርብ ነው አለ

አቤት ትራንስፖርት በሚቀጥሉት 5 አመታት 25 ሺህ በኤሌክትሪክ እና አነስተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ የ2021 የጀርመንና የሩሲያ ስሪት መሆናቸውን የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉ ደሜ ተናግረዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ ባለ 5 ፤7 እና 26 መቀመጫ ያላቸውና ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡

መግዛት የሚፈልጉ ሰዎች ከ 30 ሺህ ብር ጀምሮ የወረፋ መጠበቂያ ክፍያ በመክፈል ይስተናገዳሉ፡፡

ድርጅቱ በ7.7 ቢሊዮን ብር ካፒታል ስራውን እንደጀመረ የተገልጸ ሲሆን፣ ተሽከርካሪዎቹ የሚገጣጠሙት ደግሞ በኮምቦልቻ ከተማ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

60 ሺህ ዜጎች በቀጣዮቹ 5 አመታት በአቤት ትራንስፖርት በኩል የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply