በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ጀብውሃ ቀበሌ አሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን በአርሶ አደሮች ላይ አሁንም ጠባጫሪ ትንኮሳ እና ጥቃትን አላቆሙም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሸዋ ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ጀብውሃ ቀበሌ አሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን በአርሶ አደሮች ላይ የሚፈጽሙትን ተደጋጋሚ ትንኮሳ እና ጥቃት አለማቆማቸውን ነዋሪዎች ተናገረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት የካቲት 17/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ አሸባሪ ኦነጋዊያን በጀብውሃ ቀበሌ ሞላሌ ጎጥ በመስኖ ስራ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በፈጸሙት ተኩስ አንድ ሰው ሲቆስል፣ የገበሬዎች የጋማ እና የቀንድ ከብቶች ተገድለዋል። በአካባቢው የነበረ መከላከያ ወደ ሞላሌ አቅንቷል መባሉን ተከትሎ የወረራ ተግባር የሚፈጽሙ ኦነጋዊያን ሸሽተው መመለሳቸው ተሰምቷል።
Source: Link to the Post