#በእርግዝና ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎችበእርግዝና ወቅት እራስን ከተለያዩ ነገሮች መጠበቅ ያስፈልጋል። በእርግዝና ወቅት ከአመጋገብ ጀምሮ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ይነገራል፡፡ከአመጋገብ ጋር…

#በእርግዝና ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች

በእርግዝና ወቅት እራስን ከተለያዩ ነገሮች መጠበቅ ያስፈልጋል።

በእርግዝና ወቅት ከአመጋገብ ጀምሮ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ይነገራል፡፡

ከአመጋገብ ጋር በተያያዘም ያልበሰሉ ምግቦችን መመገብ አይመከርም ይላሉ ባለሙያዎች፡፡

እንዲሁም ያለሀኪም ትእዛዛዝ ከሚገዙ እና ከሚወሰዱ መድሃኒቶች እራሳቸውን መቆጠብ እንዳለባቸው ያነሳሉ፡፡

አንድ ነፍሰጡር በእርግዝና ግዜዋ ማድርግ ስለሚገቧት ጥንቃቄዎች እና መደረግ ስለሌለባቸው ነገሮች ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የማህፀን እና ፅንስ ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ ጋር ጣቢችን ቆይታ አድርጓል፡፡

#በእርግዝና ወቅት መደረግ ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

– የአመጋገብ ሁኔታዋን ማስተካከል (የተመጣጠነ ምግብ መመገብ)
– አተኛኘቷን ማስተካከል (በጎን በኩል መተኛት)
– በእርግዝና ግዜ ሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይመከራል ይላሉ

#መደረግ የሌለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

– በጀርባዋ መተኛት
– አልኮል መጠጦችን መጠጣት
– ማጨስ
– አነቃቂ ነገሮችን መውሰድ ይጠቀሱበታል

በእርግዝና ወቅት ባይደረጉ ይመከራሉ የተባሉ ነገሮችን አንዲት እናት የምታደር ከሆነ በፅንሱ ላይ የአፈጣጠር ችግር ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ባለሙያው ይናገራሉ፡፡

እንዲሁም አንዲት እናት በእርግዝና ወቅት አደጋ እንዳለ ማወቅ እና የትኛው ነገር አደጋ ነው የሚለው መለየት ያስፈልጋታል ፡፡

ይህም ማለት ብትደማ ፣የልጁ እንቅስቃሴ ቢቀንስ፣የሽርት ውሀ ቢፈስ ፣አቅም የሚያሳጣ እራስ ምታት ፣ ብዥታ እና ማንዘፍዘፍ የመሰሉ ችግሮች ቢገጥሟት እነዚህ ነገሮች በእርግዝና ወቅት አደጋ እንዳለ አመላካች የሆኑ ነገሮች ስለሆኑ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እንዳለባት ደ/ር ልንገርህ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply