# በእርግዝና ግዜ የሚፈጠር የባህሪ ለውጥ(behavioral changes during pregnancy)በእርግዝና ወቅት ከህመም እና ከድካም በተጨማሪ የስሜት ለውጦች መኖራቸው የተለመደ ነው፡፡ሁ…

# በእርግዝና ግዜ የሚፈጠር የባህሪ ለውጥ(behavioral changes during pregnancy)

በእርግዝና ወቅት ከህመም እና ከድካም በተጨማሪ የስሜት ለውጦች መኖራቸው የተለመደ ነው፡፡
ሁሉም እናቶች ተመሳሳይ የሆነ የእርግዝና ሁኔታ  እንደማይኖራቸውም ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡
በእርግዝና ወቅት የምግብ ፍላጎት ማጣት እና የምግብ አለመፈጨት ፣የጀርባ ህመም ፣ድካም፣በቁርጭምጭሚት እግር እና እጅ ላይ እብጠት ፣ማቅለሽለሽ  የመሰሉ ነገሮች ሊከሰቱ  እንደሚችሉም ያነሳሉ ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ነፍሰ ጡር ሴቶች በሚኖር የሆርሞን ለውጥ ምክንያት ተያይዘው የሚመጡ የባህሪ ለውጦች እንደሚያሳዩም ይነገራል፡፡
በዚህ ጉዳይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የማህፀን እና ፅንስ ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ ጋር ጣቢያችን ቆይታ አድርጓል፡፡


#በእርግዝና ጊዜ የሚፈጠር የባህሪ ለውጥ በምን ይመጣል ?

በእርግዝና ወቅት የሚፈጠሩ ብዙ ለውጦች አሉ ከነዛ ለውጦች ውስጥ  የሆርሞናል ለውጥ (የሰውነት ቅመም ) ለውጦች መሆናቸውን ያነሳሉ፡፡
ይህም ማለት በተፈጥሮ አንዲት ሴት የምታመርተው ንጥረ ነገር ወይም ሆርሞን አለ በተጨማሪ እርጉዝ ስትሆን ደግሞ እንግዴ ልጁ በተጨማሪ የሚያመርታቸው ሆርሞኖች ይኖሩና የሆርሞን መጠኑ የሚጨምርበት ሁኔታ አለ ይላሉ ባለሙያው
ለምሳሌ ኤስትሮጅን ፣ፕሮጄስትሮን የምንላቸው ቅመሞች ይጨምራሉ ፡፡በተለይ የፕሮጀስትሮን መጠን ሲጨምር አንድ ሴት መናደድን የመሰሉ ባህሪያት እንዲከሰቱ ድርሻ ይኖራቸዋል ፡፡

#የሚመጡ የባህሪ ለውጦች ምንድን ናቸው?

–  መናደድ
–  ቁጡ መሆን
–  የተከሰተው እርግዝና የሚያስጨንቃት ከሆነ ከወለደች በኋላ ጭንቀት ሊኖር ይችላል
–  ትእግስት ማጣት ይጠቀሱበታል
ይህ የባህሪ ለውጥ ከትዳር አጋራቸው ጋር ወይም ዙሪያቸው ካለው ሰው ጋር አለመግባባት እንዲፈጠር ሊያደርግ እንደሚችል ያነሱት ዶ/ር ልንገርህ እነዚህ ስሜቶች  በተፈጥሮ የሚመጡ  ስለሆኑ የትዳር አጋሮች ትኩረት ሰተው ማየት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
የማህፀን እና ጽንስ ሀኪሞችም እርግዝናው ሊያመጣ የሚችለውን ነገር በደንብ አስረግጦ በመንገር ነገሮች ከዚህ ጋር ተያያዥ እንደሆኑ እና መረዳት እንደሚያስፈልግ ሊያሳስቡ ይገባል ይላሉ

#የሚደረጉ ህክምናዎች ምንድን ናቸው?

–  ደረጃው ከፍ ካለ የሚሰጡ መድሃኒቶች አሉ
–  የስነ ልቦና ምክር እንዲያገኙ ማድረግ
–  አጠገባቸው ባለ ሰው እንክብካቤ እና ፍቅር እንዲያገኙ ማድረግ ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
በመጨረሻም በእርግዝና ወቅት የባህሪ ለውጥ ሊያጋጥም የሚችል ነገር እንደመሆኑ  የባህሪ ለውጡ የከፋ እንዳይሆን እርጉዝ እናቶች አጠገባቸው ባለው ሰው እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና ፈልገው ያመጡት ነገር ሳይሆን በተፈጥሮ  በሚከሰት የሆርሞን ለውጥ የሚመጣ ስለሆነ ይህንን  መረዳት እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ልንገርህ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት  10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply