በእሳት ቀልጦ የጠቆረ ስኳር ሰውነቱ ላይ በማፍሰስ ቁስል አስመስሎ ሲለምን የነበረ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተያዘ።
ግለሰቡ የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ልዩ ቦታው መሳለሚያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪው በእሳት ቀልጦ የጠቆረ ስኳር ሆዱ ላይ በማፍሰስ እና ቁስል እንዲመስል አድርጎ በፕላስተር በማሸግ መንገድ ላይ ተኝቶ የልመና ተግባር ሲያከናውን የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው መረጃውን ለፖሊስ ያደረሱት።
በየካ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ግለሰቡ ምንም አይነት የጤና ዕክል ሳይኖርበት በማታለል ገንዘብ ለመሠብሰብ የተጠቀመበት ዘዴ መሆኑን ፕላስተሩን ከሆዱ ላይ በማስላጥ ማረጋገጥ ችለዋል ብለዋል።
በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ድጋፍ የሚጠይቁ ግለሰቦች ቢኖሩም ልዩ ልዩ የማታለያ ዘዴዎችን ተጠቅመው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ገንዘብ የሚለምኑ ሰዎች እያጋጠሙ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን የማረጋገጥ ስራ በመስራት አታላዮችን ሊያጋልጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።
ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos