You are currently viewing በእስራኤል “እኔም ፋኖ ነኝ፣ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ ግድያ፣አፈና፣ እስር እና ማሳደድ ይቁም” በሚል ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በእስራኤል “እኔም ፋኖ ነኝ፣ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ ግድያ፣አፈና፣ እስር እና ማሳደድ ይቁም” በሚል ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በእስራኤል “እኔም ፋኖ ነኝ፣ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ ግድያ፣አፈና፣ እስር እና ማሳደድ ይቁም” በሚል ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእስራኤል “እኔም ፋኖ ነኝ፣ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ ግድያ፣አፈና፣ እስር እና ማሳደድ ይቁም” በሚል ግንቦት 26/2014 ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገው በእስራኤል ሀገር ኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አገዛዝን ክፉኛ አውግዘዋል። በዚህ በኢትዮጵያ የጊዜ አቆጣጠር ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍም የአማራ ፋኖን የሚደግፉና የመንግስትን የአፈና አካሄድ የሚያወግዙ ሰልፈኞች ተሳትፈውበታል። በ እስራኤል ቴላቪቭ የተደረገውን ይህን የተቃውሞ ሰልፍ:_ የአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል፣ ከአብን ድጋፍ ሰጭ አባላት በእስራኤል፣ ከምጽአተ አማራ እና ከሌሎች የወገናቸው ግፍ እና በደል ካንገፈገፋቸው ሀገር ወዳድ አማራዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑን ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ቆይታ ያደረጉት ከአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ከሆኑት አቶ ደርበው ብርቁ ተናግረዋል። በተቃውሞ ሰልፉም በዋነኝነት የሚከተሉት መልዕክቶች ተላልፈዋል:_ 1) በህግ ማስከበር ስም በአማራ ላይ የተከፈተውን መንግስታዊ ግድያ፣አፈና፣እስር፣እንግልትና መሳደድ ይቁም! 2) በፋኖ ላይ የተከፈተው ይፋዊ ጦርነት ይቁም! በተለይም በመርዓዊ፣በሞጣ፣በወልድያ እና በሀርቡ የተፈጸመውን ይፋዊ ጦርነት እናወግዘዋለን፤ በንጹሃን አማራዎች ላይ ግድያ የፈጸሙ፣እስር፣ወከባ እና እንግልት የፈጸሙ አካላት በህግ ከተጠያቂነት አያመልጡም፤ 3) በአፈና ላይ ያሉ ወገኖች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ፣ 4) የአማራ ፋኖን ብሎም የመላ አማራን ቅስም ለመስበር ታልሞ እየተፈጸመ ያለው የተደራጀው መዋቅራዊ በደል ይቁም! 5) በወልቃይት፣በጠገዴ፣በራያ እና በሌሎች የአማራ አጽመ እርስቶች ላይ በመንግስት የሚደረጉ ግልጽነት የጎደላቸው ድርድሮች ህዝቡንና የሚመለከታቸው አካላት እስካላካተቱ ድረስ መቼም ተቀባይነት አይኖራቸውም። 6) ከአዲስ አበባ ጋር በተያያዘ በባልደራስ አመራሮችና አባላት የሚደረገው ተደጋጋሚ እስር እና ወከባ አላማው ግልጽ ስለሆነ አጥብቀን እንቃወመዋለን፤ በአስቸኳይ እንዲቆምም እንጠይቃለን። 7) በተላላኪው ብአዴን እንዲሁም በአብን ድክመት የተነሳ በአማራ ህዝብ ላይ ግፍ እና በደሉ ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ የገለጹት ሰልፈኞች አብን በአስቸኳይ የአመራር ሪፎርም እንዲያካሂድ እንጠይቃለን ብለዋል። ብአዴን ካለፉት በርካታ ዓመታት ጀምሮ አሁንም ድረስ ጌታ በመቀየር እየሄደበት ያለው መንገድ አይለወጤ መሆኑን ስለሚያሳይ ህዝባዊ ትግሉ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል፤ እስካሁን በአማራ ህዝብ ላይ ለደረሰው ሁለንተናዊ ጥቃት መቼም ቢሆን ከተጠያቂነት አይድንም ብለዋል። 8 በጋዜጠኞችና በጋዜጠኝነት ላይ የተከፈተው አሳፋሪና አሳዛኝ ጥቃት ይቁም! በጋዜጠኞች፣በአክቲቪስቶች፣በፖለቲከኞችና በሌሎች ንጹሃን አማራዎች ላይ የቀጠለው ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን። “ሳናጣራ አናስርም” የሚለው ቃል በተግባር “አስረን እናጣራን” እንዲሁም “አፍነን ደብዛ እናጠፋለን” መሆኑን ተገንዝበናል። 9) አርሶ አደሩ ወደ እርሻ በሚሰማራበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ይህ የዘመቻ ጥቃት መከፈቱም ባለፉት ወራት በጦርነት የደቀቀው ህዝብ እንዳያለማ እና በርሃብ እንዲቀጣ ብሎም ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ እንዲገጥመው ታቅዶ እየተሰራ ስለመሆኑ አመላካች ነው፤ ይህ አፍራሽ መንግስታዊ አካሄድ በአስቸኳይ ይቁም! 10) በሞጣ ፋኖ ነህ በሚል የተገደለው የ13 ዓመት ህጻን ልንገረው አዲስ ሁኔታ፣ የጁቤ ላይ በመቶ አለቃ አበበ እንዬው የ4 ዓመት ህጻን ልጅና በባለቤቱ ላይ የተፈጸመውን እስር እና እንግልት እንዲሁም ከተከራዬችበት ቤት እንድትወጣ መደረጉን አጥብቀን እናወግዛለን፤ በሀርቡ እስር ቤት በተፈጸመበት ድብደባ የተገደለው የፋኖ ሲራጅ መሀመድ ጉዳይም በእጅጉ እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ገዳዮች በህግ እንዲጠየቁም ጥሪ አድርገዋል። 11) የኦሮሙማ መስፋትና መንሰራፋት ይቁም፤ ወረራ ይቁም። ከ21ኛ ክፍለ ዘመን ወደ 16ኛ ክፍለ ዘመን ለመቀየር በአማራ ብሎም በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደረገውን የተደራጀ የኦሮሙማ እና የገባሪዎቻቸውን እንቅስቃሴ እንቃወማለን። 12) በእምነቶች መካከል የሚደረግ ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ በመከፋፈል እና በማጋጨት በደም መነገድ፣ስልጣን ለማራዘም የሚደረግን የከንቱዎች እንቅስቃሴ እናወግዛለን፤ እንዲቆምም እንጠይቃለን። በመጨረሻም መንግስት በሀገረ እስራኤል እና በሌሎች ሀገራት የወጡ ሰልፈኞች ባነሷቸው ጉዳዮች ዙሪያ በአስቸኳይ ምላሽ በመስጠት እስካላስተካከለ ድረስ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይታወቅልን የሚል ጥብቅ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply