በእስር ላይ የሚገኙት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ተዘግቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእስር ላይ የ…

በእስር ላይ የሚገኙት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ተዘግቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእስር ላይ የሚገኙት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ተዘግቷል። የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሐምሌ 19/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት “ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል በመናድ ሽብር” የተጠረጠሩት በእነ ፋኖ ቴዎድሮስ ጌታቸው መዝገብ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይን ዘግቷል። መዝገቡ የተቀጠረው መርማሪ ፖሊስ ማስረጃዎችን ለማቅረብ በተሰጠው ጊዜ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ ተቋማት የሠበሠብን ቢሆንም ሌሎች ማስረጃዎች ይቀሩናል በማለቱ ቀሪ ማስረጃዎች ለመሠብሰብ የ10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ በሰጠው መሰረት ነው። በዋለው ችሎትም መርማሪ ፖሊስ ያሰባሰባቸውን ማስረጃዎችን ገልጾ ሌሎች ቀሪ ማስረጃዎቸን አሰባስቤ ስላልጨረስኩ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ተከራክሯል። የተጠርጣሪዎች ጠበቃ በበኩላቸው ቀሩን ያሏቸው ማስረጃዎች ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ስለሆኑና በቂ የጊዜ ቀጠሮ ስለተሰጣቸው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አስፈላጊ አይደለም ብለው ተከራክረዋል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ ለምርመራ 24 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ስለተሰጠና የሚመጡ ማስረጃዎች ከመንግስት ተቋማት ስለሆነ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አያስፈልግም በሚል የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ ዘግቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply