በእስር ላይ የሚገኙ አባላቱ ካልተፈቱ ከሃገራዊ ምክክሩ ራሱን ለማግለል እንደሚገደድ ኢህአፓ ገለጸ፡፡

ፓርቲው በአሁኑ ወቅት ሰባት የሚሆኑ አባላቱ ጦርነት ይቁም ሰላም ይስፈን የሚለውን ሰልፍ በማስተባባርና በሌሎችም ምክንያቶች ታስረው እንደሚገመኙ ለኢትዮ ኤፈ ኤም ተናግሯል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ህዳር 30/2016 ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም መሰረዙ ይታወሳል፡፡

የኢህአፓው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ አብርሃም ሀይማኖት እንደሚሉት ግን ከዛም በኋላ የፓርቲው አባላት እየታሰሩ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም የፓርቲውን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ እና ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆነቱ አቶ አበራ ንጉስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህ አካላት የማይፈቱ ከሆነ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አሳስበዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply