You are currently viewing በእነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ እና በሌሎች ሶስት ፋኖዎች ላይ ከተፈጸመው አፈና በኋላ አድራሻቸውን በትክክል ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ…

በእነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ እና በሌሎች ሶስት ፋኖዎች ላይ ከተፈጸመው አፈና በኋላ አድራሻቸውን በትክክል ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ…

በእነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ እና በሌሎች ሶስት ፋኖዎች ላይ ከተፈጸመው አፈና በኋላ አድራሻቸውን በትክክል ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከባህር ዳር ምንጮችን ለማነጋገር የሞከረ ሲሆን ጥቅምት 2/2015 አፈና የተፈጸመባቸው የእነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ እና ሌሎች ሶስት ፋኖዎች አሁን ላይ ያሉበትን ተጨባጭ አድራሻን ለማወቅ አልተቻለም። ምንጮች እንደሚሉት ፋኖ ናትናኤል ዘነበ፤ ጥላሁን አበጀ ፤የሽዋስ ገነት፤ ቢያድግ በላይ በባህር ዳር ቀበሌ 11 በሚገኘው የልዩ ኃይል ካምፕ ታስረው እንዳደሩ እና እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዛው በካምፑ ውስጥ ነበሩ። ይሁን እንጅ ከሰዓት በኋላ እነ አርበኛ ጥላሁንን ወደ ባህር ዳር ቀበሌ 16 በሚገኘው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዳዘዋወሯቸው የገለጹም አሉ። አንዳንድ የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ አመሻሹን ፍ/ቤት ልንወስዳችሁ ነው በሚል ከ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዳስወጧቸው ብሎም ፍ/ቤት ከወሰዱ በኋላ ወደ ሰባታሚት ማ/ቤት እንዳዘዋወሯቸው ያመለክታል። ይሁን እንጅ አሁንም በሰባታሚት ማ/ቤት ስለመግባታቸውም እርግጠኛ ለመሆን አልተቻለም። በሌላ በኩል በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን፣ ስለአማራ ህዝብ ሲል ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ያለውን አርበኛ ዘመነ ካሴን የባህር ዳር እና የአካባቢው ነዋሪዎች በችሎት እየተገኙ ድጋፋቸውን ከማሳዬት በተጨማሪ ሁሌም ማ/ቤት ተገኝተው በመጠየቅ፣ በማበረታታት እና በመጠበቅ ከመቼም ጊዜ በላይ ከጎኑ እንዳይለዩት የሚጠይቁ እና የሚያሳስቡ መልዕክቶችም ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) እየደረሱት ይገኛል። ከህግ እና ስርዓት ውጭ በመሆን ሰዎችን ማፈንና ማሸበር የስርዓቱን እድሜ ለማሳጠር ይረዳ ካልሆነ በስተቀር አንዳችም የሚያመጣው ለውጥ እንደማይኖር በመገንዘብ ስርዓታዊ አፈናው እንዲቆምም ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply