
በእነ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ቤት ፍተሻ ተደርጓል፤ ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አንድም ነገር አልተገኘም ተብሏል። መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፌደራል ፖሊስ መጋቢት 20/2015 ረፋድ ላይ በእነ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ቤት ፍተሻ አድርጓል። ነገር ግን ጋዜጠኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አንድም ነገር አልተገኘም ተብሏል። በጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ አራት የፌደራል ፖሊስ አባላት የዐይን እማኞችን ከጎረቤት በማካተት ፍተሻውን አድርገው ተመልሰዋል ተብሏል። የሮሃ ኒውስ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና የአማራ ድምጽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ መጋቢት 17/2015 በፌደራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው ወደ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸው አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አረጋግጧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post