You are currently viewing በእንጅባራ ከተማ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ለጉብኝት ከከተማ በወጡበት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የህይወት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 22 ቀን 20…

በእንጅባራ ከተማ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ለጉብኝት ከከተማ በወጡበት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የህይወት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 22 ቀን 20…

በእንጅባራ ከተማ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ለጉብኝት ከከተማ በወጡበት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የህይወት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከእንጅባራ ከተማ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎችን ይዞ ለጉብኝት የወጣ መኪና ባጋጠመው የትራፊክ አደጋ የ4 ሕጻናት ተማሪዎችና የአንድ መምህር ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የእንጅባራ ኮሙኒኬሽን የትራፊክ አደጋው መድረሱን የሚያረጋግጥ መረጃ በገጹ የለጠፈ ቢሆንም፣ ዝርዝር መረጃ አላወጣም፡፡ አደጋው ያጋጠመው “ዳሳሽ አካዳሚ” በተባለ የሕጻናት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ሕጻናቱ በሰርቪስ መኪና “ዶንደር ፏፏቴ” ወደ ተባለ ቦታ መጋቢት 22/2015 ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ለጉብኝት ከከተማ ወጥተው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ የትራፊክ አደጋው ከባድ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ እስካሁንም የ3 የሕጻናት ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉና፤ አንድ ሕጻንና እና አንዲት መምህርት ወደ ሕክምና እንደደረሱ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ህጻናት መኖራቸውም የተጠቆመ ሲሆን፤ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ህጻናት በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ወደ ሕክምና ከገቡት መካከልም 4ቱ አገግመው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸው ተነግሯል ሲል ያጋራው አዲስ ማለዳ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply