በእንግሊዝ ነርሶች አድማ መቱ

https://gdb.voanews.com/c260b496-5124-4c4d-a1a5-87142e0efac0_w800_h450.jpg

በእንግሊዝ የሚገኙ ነርሶች በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ደሞዝ እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ የተመታ አድማ መሆኑ ተነግሯል። 

የሮያል ኮሌጅ የነርሶች ማኅበር 100 ሺህ ነርሶች አድማውን እንደተቀላቀሉ አስታውቆ፥ መንግስት በ48 ሰዓት ውስጥ መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ በሚቀጥለው ወር ሌላ አድማ እንደሚጠራ አስጠንቅቋል። 

የሰራተኛ ማኅበሩ ከዋጋ ግሽበቱ 5 በመቶ ከፍ ያለ ጭማሪ ቢጠይቅም፣ መንግስት ያንን ማድረግ እንደማይችል አስታውቋል። 

የነርሶቹ አድማ የተደረገው በሌሎች የሥራ መስኮች ያሉ ሠራተኞችም ከደመዎዝ ጭማሪ ጋር በተገናኘ እርምጃ ለመውሰድ በሚዘጋጁበት ወቅት ነው። 

የአምቡላንስ፣ የባቡር እና የፓስፖርት ቢሮ ሠራተኞችም የሥራ ማቆም አድማ መጥራታቸው ታውቋል። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply