በእንግሊዝ የሚገኙ ተመራማሪዎች የካንሰር በሽታን ለማከም ያስችላል ያሉትን የካንሰር ክትባት አስተዋውቀዋል:: ይህ ክትባት በሰው ልጅ የምርምር ሂደት ውስጥ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እንደሆነም…

በእንግሊዝ የሚገኙ ተመራማሪዎች የካንሰር በሽታን ለማከም ያስችላል ያሉትን የካንሰር ክትባት አስተዋውቀዋል::

ይህ ክትባት በሰው ልጅ የምርምር ሂደት ውስጥ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እንደሆነም ነው የተገለጸው::
የክትባቱ ህክምና በመጀመሪያ የሚያተኩረው የአንጀት፣ የጣፊያ፣ ቆዳ፣ ሳንባ፣ ፊኛ እና የኩላሊት ካንሰር ህመምተኞች ላይ ነው ተብሏል::

ለካንሰር ህመም ፈውስ ይሆናል የተባለው አዲሱ ክትባት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓትን በማጎልበት ላይ የተመሰረተ ህክምና ለመስጠትየሚያስችል መሆኑ ተነግሯል::
የሙከራ ክትባቱን የወሰደው የመጀመሪያው ታካሚ የ55 አመቱ የኮሎሬክታል ካንሰር እጢ ቀዶ ጥገና የተደረገለት እና ኬሞቴራፒ ሲወስድ የነበር መሆኑ ተገልጿል::

“በእንግሊዝ ታካሚዎች ለአንጀት ካንሰር የሚሆን ክትባትን ማግኘት መጀመራቸው በጣም የሚያስደስት ነው” ሲሉ በእንግሊዝ የካንሰር ምርምር እና ፈጠራ ስራ አስፈፃሚ ኢየን ፉልክስ ተናግረዋል።
በኤምአርኤን ላይ የተመሰረቱ ክትባቶችን መጠቀም እና ካንሰርን በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች መለየት እንዲሁም ማዳከም የሚችል ነውም ተብሏል።

ይህ ህክምና ከቀዶ ጥገና፣ ከኬሞቴራፒ እና ከሬዲዮ ቴራፒ ጋር በመሆን የካንሰር በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል
ክትባቱ ከተሳካ የአንጀት ካንሰርን መከሰትና መመለስን ለመከላከል ትልቅ አበርክቶ የሚኖረው “ጨዋታ ቀያሪ” ይሆናል ተብሏል ሲል ኒውስ ዊክ ዘግቧል::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply