You are currently viewing በእውነቱ ይኸን ግፍ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብሎ ማለፍ  ሀላፊነት የጎደለው ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች ከገዢው የአብይ አህመድ የኢምባሲ ሹሞች ጋር እስከዛሬ ሲያደርጉ የነበረ…

በእውነቱ ይኸን ግፍ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብሎ ማለፍ ሀላፊነት የጎደለው ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች ከገዢው የአብይ አህመድ የኢምባሲ ሹሞች ጋር እስከዛሬ ሲያደርጉ የነበረ…

በእውነቱ ይኸን ግፍ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብሎ ማለፍ ሀላፊነት የጎደለው ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች ከገዢው የአብይ አህመድ የኢምባሲ ሹሞች ጋር እስከዛሬ ሲያደርጉ የነበረውን ግንኙነት እንዲያቆሙ በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን በጀርመን ሀገር ከምንኖር የአምሀራ ተወላጆች የጋራ መድረክ የተሠጠ መግለጫ!! የአማራ ሚዲያ ማእከል… ሐምሌ 5 2014 አ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጀርመን ሀገር ግዛቶች( Sates) ለምትገኙ የክርስትና እና የእሥልምና የኃይማኖት ተቋማት በሙሉ ! እንደሚታወቀው በሀገራችን በኢትዮዽያ በአሁኑ ወቅት እጅግ የከፋ የሕዝብ ዕልቂት እየደረሰ ነው፣በተለይም በአምሀራው ህዝብ ላይ በማንነቱ ብቻ ጭፍጨፋ ንብረት መውደምና ከቀዬው መፈናቀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየከፋና እየጨመረ መምጣቱ እጅግ ልብን የሚሰብርና የሚያሳዝን ነው!! የቀደምትና የረጅም እድሜ የታሪክ በለጠጋ የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ችግር ብቻ ሳይሆን በሰው ሠራሽም ችግር ምክንያት ዜጎቿ ከፍተኛ የሆነ መከራና ጉዳት እየተፈራረቅባቸው አንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው የደርግ ሥርዓት አልፎ ወያኔ ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሕዝብ ላይ በተለይም በአምሀራው ነገድ ላይ በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍል የሚፈፀመው ጥፋት ያለምንም ጠባቂና ተከላካይ ከሚገባው በላይ ተባብሶ ቀጥሏል ከዚሕም የተነሳ እኛ፣ 1. ሠው በመሆናችን 2. በግፍ የሚጨፈጨፈው ነገድ ልጆች በመሆናችን ልባችን በሐዘን እጅጉን ተሰብሯል። በህወሓት የበላይነት ይዘወርና ይመራ የነበረው ኢህአዴግ ቁጥር አንድ ሥልጣን ለቋል ተብሎ በይፋ ሲነገር ደስ ብሎንና ሁላችንም እኩል እንደ ዜጋ የምንታይበት በሁሉም የሐገሪቱ ክፍል በነጻነትና በእኩልነት በሕግ የበላይነትና ጥላ ስር የሚመራ የተሻለ ነገር ሥንጠብቅ.. ” በኦሕዴድ ኦነግ መራሹ ኢሀዴግ” ቁጥር ሁለት” (ብልጽግና) የሚባል ጨካኝ ስብስብ(confuser) ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በተለይ በአምሀራው ነገድ ብሎም በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረስ ያለው ግድያ ከቦታ ቦታ መፈናቀል በብዙ እጥፍ እና እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም!!! እኛ የአምሀራ ተዎላጆች የጋራ መድረኩ ቅሬታና ትዝብት፣ በጀርመን ሀገር በተለያዩ ግዛቶች (States) ከተሞችና ግዛቶች ለምትገኙ የቤተ-እምነቶችና የኢትዮጵያውያን ማህበራት ፣ በተለይ የሐይማኖት ተቋማት ክርስቲያንም ይሁን ሙስሊም፣ የተቋቋማችሁበት አውድ “የቅዱስ መጽሀፍንና የቅዱስ ቁራንን” የአምላክን ቃል አስተምህሮና መርሕ ማለትም “ፍቅርንና ፍትሕን” ለሚሠማችሁ ማሕበረ-ሰብ ማስተማርና ህዝቡም በተግባር የህይወቱ መመሪያ ማድረግ ነው !! ነገር ግን የእምነቱን መርህ ዘንግታችሁ (ድሀ ተበደለ ፍትህ ተጓደለ የሚለውን ተላልፋችሁ)፣የዜጎችን ሰብዓዊ መብት እየገፈፈ ያለን፣ ዘረኝነትን በገሃድ በማናለብኝነት የሚያስፋፋውንና ጽንፈኞችን ከጀርባ ሽፋን ሰጥቶ እያስታጠቀ ንጹሃን ወገኖቻችንን በግፍ እያስጨፈጨፈ ያለን አምባገነን መንግስት ወጥቶ በማውገዝ እና ከህዝባችን ጎን አለመሆን ከትዝብት ባሻገር አሳፋሪና በታሪክ የሚያስወቅስም ጉዳይ ሁኖ አግኝተነዋል ይሕም ፈጽሞ ግብዝነት ነው። በእውነቱ ይኸን ግፍ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብሎ ማለፍ ሀላፊነት የጎደለው ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች ከገዢው የአብይ አህመድ የኢምባሲ ሹሞች ጋር እስከዛሬ ሲያደርጉ የነበረውን ግንኙነት እንዲያቆሙ በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን። በሕዝብ ሞት በአስከሬኑም ከሚቀልድ የገዢው መንግሥት ሹሞች ጋር የሚካሄድ ግንኙነነት በፍፁም ጤናማ ባለመሆኑ መስተካከልም እንዳለበት አበክረን እናሳውቃለን። በተለይ የቤተክህነት አስተዳዳሪዎች የሆኑ በዚህ አንገብጋቢ ወቅት ከህዝቡ ጎን በመሆን ይህን አስከፊ ስርአት እና በዘር ላይ የተመሰረተውን የአገዛዙን ህገ-መንግስት ማውገዝ አለመቻላቸው በእነርሱ ላይ የነበረንን አመኔታ እንድናጤነው ከማድረጉም በላይ በዕምነታችን ላይ ያለን ተስፋ እየተሸረሸረ እንዲኼድ ምክንያት እየሆኑም ነው። ስለሆነም ሀገራችንን በአሁኑ ሰአት ከውድቀት ለማዳንና የዜጎችን ሰብዓዊና የዜግነት መብት እንዲከበር፣ የዘረኝነት አጥፊ ተግባር እንዲወገድ ሁላችንም ባለን አቅምና ችሎታ ተቻችለንና ተደጋግፈን በመተባበር እጅ ለእጅ ተያይዘን መቆምና አብሮ መስራት አማራጭ የሌለው ወቅታዊና ሃገራዊ ጥሪ ነው ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡ ስለዚህም በቀጣይ በሚኖሩን የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በመገኘት ጭፍጨፋውን በማውገዝ ፣ ለሀገር እና ለህዘብ በጋራ እንድንቆም፣ በግፍ እየተፈጀ ያለውን የአማራን ህዝብ በየቦታው ጥቃት የሚደርስባቸውን ወገኖቻችንን ሰቆቃና ፍጅት ለማስቆም በሚደረግ ሁለገብ ትግልና ጥረት አብረን ለሠላም፣ ለሰብዓዊ መብት እና ለፍትህ እንድንቆም ከህዝባችን ጎንም እንድንሰለፍ ይህን ጥሪ በአክብሮት እናቀርባለን። የአማራ ተወላጆች የጋራ መድረክ በጀርመን

Source: Link to the Post

Leave a Reply