
በእውነት ይኸ ግፍ የት ያደርሰን ይሆን?የዩኒቨርስቲ መምህር እና የአዲስአበባ ም/ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እኔ እንደግለሰብ እየደረሰብኝ ያለ በደል አይደለም የሚያሳስበኝ። የሚያሳስበኝ ተቋማዊ፣ ስርአታዊ የሆነው የአማራ ህዝብ በደል ነው። በእኔ ላይ እየሆነ ያለው አንድ ማሳያ ነው። ነገር ግን እንደህዝብ አደጋ ላይ ነን። አማራ ስትሆን እውነትን ማውራት የለብህም። ግፍና በደልን ማውገዝ የለብህም። ሁሉን አሜን ብለህ መቀበል ነው የሚጠበቅብህ። ከዚህ ውጭ በመርህ፣ በፕሪንሲፕል ልመራ ብትል፣ እውነትን ልያዝ ብትል፣ ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለእኩልነት ልታገል ብትል፣ በተማርከው ዲሲፕሊን ልመራ ብትል ጽንፈኛ ተብለህ ይዘመትብሃል። በቃ ይኸው ነው እየሆነ ያለው። በራሴ ላይ የደረሰንና እየደረሰ ያለን እውነት ነው የማወራው። በዚህ ሁኔታ በሀሳብ ተግባብቶ ለውጥ ለማምጣት አይቻልም። ሀገሪቱም አልታደለችም፣ እኛም አልታደልንም። ተስፋ ያስቆርጣል ብለዋል!!! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post