
በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦቦሳንጆ የተመራው የአፍሪካ ኅብረት ልዑካን ሐሙስ ኅዳር 15/2015 ዓ.ም. ባደረጉት የመቀለ ጉብኝት ከህወሓት አመራሮች ጋር ተነጋገሩ። የፕሪቶሪያውን ግጭት በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀለን የጎበኘው የልዑካኑ ቡድን፣ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፑምዚሌ ማላምቦ-ናኩክ እና የኅብረቱ የፖለቲካ፣ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዮን አካቷል።
Source: Link to the Post