በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ኮሌራ አሁንም እንደቀጠለ ነው – ተመድ

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-b14c-08dae2e9e855_tv_w800_h450.jpg

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ተከስቶ የነበረዉ የኮሌራ በሽታ  ወደ አጎራባች ዞኖች እየተስፋፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ( ኦቻ) ገለፀ።

በባሌ ዞን አምስት ወረዳዎችና በአጎራባች የሶማሌ ክልል የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ ጉጂ ዞን፣ ግርጃ ወረዳ መስፋፋቱንም ድርጅቱ ትላንት ባወጣዉ መግለጫ አመልክቷል ።

ከሰባት መቶ አርባ ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታዉ መጋለጣቸውንም ድርጅቱ የጠቆመ ሲሆን የኦሮሚያ ጤና ቢሮም በሽታውን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply