በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልል ያለዉ የሰላም ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ አስታወቀ።በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ…

በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልል ያለዉ የሰላም ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ አስታወቀ።

በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር መሰረት አሊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግጋረዋል።

በአካባቢዉ ኢንተርኔት እና ስልክን ጨምሮ መረጃ የማግኘት መብት ከተገደበ ዓመታትን ያሳለፈ ነው የሚሉት ዳይሬክተሯ፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አሰጊነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ብለዋል።

ዛንዚባር ላይ የተደረገዉ የሰላም ንግግር ተሰፋ የተጣለበት ቢሆንም መፍትሄ እስካሁን አላመጣም የሚሉት ዳይሬክተሯ፣ አሁንም ሁሉንም የሰላም አማራጮች በመጠቀም ዘላቂ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል ነው ያሉት።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልልም ከደቡብ ሱዳን ተፈናቅለዉ የመጡ ፍልሰተኞች፣ በክልሉ ያሉ ዜጎችን ከቦታቸዉ በማስወጣት ነዋሪዉ ምንም አቅም እንዳይኖረዉ አድርዉታል ሲሉ ገልፀዋል።

እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተበራክተዉ የቀጠሉት በተለይም በመንግስት በኩል እሳት የማጥፋት እንጂ፣ ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ባለመስጠት በመሆኑ መንግስት ለሀገራዊ ምክክር ሀላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለ2016 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ “ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር መታረቃችን አይቀሬ ነው፡፡” ማለታቸዉ አይዘነጋም፡፡

በአቤል ደጀኔ

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply