You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለእስር ተዳረጉ‼️              ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም               አሻራ ሚዲያ ፣ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ሀገ…

በኦሮሚያ ክልል ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለእስር ተዳረጉ‼️ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ሀገ…

በኦሮሚያ ክልል ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለእስር ተዳረጉ‼️ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ወንድወሰን ጥላሁን በትናትናው ዕለት ምሽት ላይ በክልሉ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸው ተገጿል።በተያያዘ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መ/ር ሰለሞን ዘገየ በመንግስት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሠራቸው ታውቋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በጉዳዩ ላይ ለካቢኔያቸው ሰጡት በተባለውና በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ በተላለፈው ዝግጅት ‘መንግሥት ከየትኛውም ወገን ገለልተኛ ነው’ ማለታቸው ይታወሳል። የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በልዩ ልዩ የቋንቋ አገልግሎት በኦሮምኛና በሲዳማ አዋሳኝ ወረዳዎች የሲዳመኛ ቋንቋ የወንጌል አገልግሎት የሚሰጥበት ሀገረ ስብከት ነው። ምንጭ :- EOTC “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply