በኦሮሚያ ክልል ሱሉልታ ከተማ ከህግ ውጭ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ ነዉ ተባለ፡፡በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተመሰረተዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቃሶ በተባለዉ አካባቢ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/edgpMf62TeEwOussffaBH2xtV5C6XHEgRnK217bFsXJKWR0N-vrlnJ54lY0QyKJMa9RvD9pJYhHnwEtbx2vX4JJWgGLfTh0d_l10uaCJh5dQujJDlNL_akVF1RCGJAv45NvN_Ft72n3wnhc70V0ydnwkMuiZQoYRFIOguiGp5uVaa5a8wWPprE7X6UmeLDZl1iYgQq7MSpkkU4pZV1NQakpmjWQXj-1DtPHvT5Vjds_e8RV4yZ0Xct0WL1ZJCTl4RhLDXAY5sgXlQZZjD7wV9BIDg_ls6pQJsx1tr-F9q12TsH2MxotpvER6EdjNAo3S4nR9FGAwcmK89UodAH9J6Q.jpg

በኦሮሚያ ክልል ሱሉልታ ከተማ ከህግ ውጭ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ ነዉ ተባለ፡፡

በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተመሰረተዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቃሶ በተባለዉ አካባቢ፣ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፣ ልዩ ስሙ ቃሶ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ “መጤ ናችሁ በሚል ቤታችን እየፈረሰብን ነዉ” ብለዋል፡፡
ቤት ንብረት አፍርተዉ በአካባቢዉ መኖር ከጀመሩ ከ5 አመት እስከ 10 አመት ድረስ እንደሆናቸዉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ያለንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸዉ እንደፈረሰ ነግረዉናል፡፡

ዜጎቹ የሚመለከተዉ አካል እንዲያስቆምላቸዉ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸዉ ገልፀዋል፡፡
በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸዉን አንስተዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የአካባቢዉ የደንብ አካላት የሚፈርሱ ቤቶችን እየለዩ መሆናቸዉንም ሰምተናል፡፡
በመሆኑም መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸዉን አሰተላልፈዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ምላሽ እንዲሰጠን ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 07 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply