በኦሮሚያ ክልል በ8ወራት ዉስጥ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ቫይረስ መያዛቸዉ ተገለጸ፡፡ባለፉት 8 ወራት በክልሉ ከተደረገ 1.8 ሚሊየን አከባቢ ምርመራ ከ6ሺህ 4መቶ15 በላይ ሰዎች ቫ…

በኦሮሚያ ክልል በ8ወራት ዉስጥ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ቫይረስ መያዛቸዉ ተገለጸ፡፡

ባለፉት 8 ወራት በክልሉ ከተደረገ 1.8 ሚሊየን አከባቢ ምርመራ ከ6ሺህ 4መቶ15 በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ተገኝቷል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ በክልሉ ወደ 158 ሺህ ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸዉ ዉስጥ ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት ነግረዉናል፡፡

ከእነዚህ መካከል ደግሞ ወደ 128ሺህ6መቶ48 የሚሆኑት የኤች አይ ቪ መድሃኒት ተጠቃሚ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

በክልሉ ቫይረሱ አለባቸዉ ከተባሉት መካከል 97 በመቶዎቹ በደማቸዉ ዉስጥ ያለዉ የቫይረስ መጠን ዝቅ ማለቱንም ነግረዉናል፡፡

በክልሉ ያለዉ የስርጭት ምጣኔ ወደ 0.3 በመቶ ነዉ ያሉት ዶ/ር ጉሻ፤ በከተሞች አከባቢ ግን ወደ 3 በመቶ ከፍ እንደሚል ነግረዉናል፡፡

በክልሉ እንደ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ እና ቢሾፍቱ ያሉ አከባቢዎች ላይ የስርጭት ምጣኔዉ ከ2-3 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑንም ነግረዉናል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply