
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶች እና በጥቃቶች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች እና መፈናቀሎች እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሆኑ በርካታ አመላካቾች እንዳሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በክልሉ ዞኖች በተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን በጠቀሰበት የስድስት ወር ግምገማው ነው ኢሰመኮ የገለጸው።
Source: Link to the Post