በኦሮሚያ ክልል ወደ 158ሺህ ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸዉ ዉስጥ አለ ተብሎ እንደሚገመት የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ባለፉት 6 ወራትም 7ሺህ አዳዲስ ሰዎች በኤች አይ ቪ መያዛቸዉ ተገ…

በኦሮሚያ ክልል ወደ 158ሺህ ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸዉ ዉስጥ አለ ተብሎ እንደሚገመት የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ባለፉት 6 ወራትም 7ሺህ አዳዲስ ሰዎች በኤች አይ ቪ መያዛቸዉ ተገልጿል፡፡

ባለፉት 6 ወራት በክልሉ ከተደረገ 2 ሚሊየን አከባቢ ምርመራ 7ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ተገኝቷል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ በክልሉ ወደ 158 ሺህ ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸዉ ዉስጥ ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት ነግረዉናል፡፡

ከእነዚህ መካከል ደግሞ ወደ 126ሺህ6መቶ80 የሚሆኑት የኤች አይ ቪ መድሃኒት ተጠቃሚ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

በክልሉ ያለዉ የስርጭት ምጣኔ ወደ 0.6 በመቶ ነዉ ያሉት ዶ/ር ጉሻ፤ በከተሞች አከባቢ ግን ወደ 3 በመቶ ከፍ እንደሚል ነግረዉናል፡፡

የኤች አይ ቪን መድሃኒት በተመለከተ የሚደርሰዉ የመድሃኒት አቅርቦት ‹‹ከሞላ ጎደል ጥሩ ነዉ››ያሉት ሃላፊዉ አልፎ አልፎ የመድሃኒት መቆራረጥ ይከሰታል ብለዉናል፡፡

‹‹ኤች አይ ቪ በጣም ሴንሴቲቭ ነገር ነዉ›› ያሉት ሃላፊዉ ፤ መድሃኒቱን ለሁለት ቀናት እንኳን ማቋረጥ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚታወቅ ነዉ ብለዋል፡፡

በ2015 የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት የመድሃኒት አቅርቦት መቆራረጥ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር ያሉት ዶ/ር ጉሻ ፤በዚህኛዉ ዓመት ግን ብዙም ችግር እንዳልነበር ነግረዉናል፡፡

በክልሉ እንደ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ እና ቢሾፍቱ ያሉ አከባቢዎች ላይ የስርጭት ምጣኔዉ ከ2-3 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑንም ነግረዉናል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply