በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም ተጠየቀ፤ የምስራቅ ወለጋ አማራዎች በላኩት ደብዳቤ መንግስት መሩ ጥቃት ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ አመላክ…

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም ተጠየቀ፤ የምስራቅ ወለጋ አማራዎች በላኩት ደብዳቤ መንግስት መሩ ጥቃት ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ አመላክተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ፦ ከምስራቅ ወለጋ ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ እና አካባቢዋ የምንገኝ የአማራ ብሔር ተወላጆች ለሁለት ዓመት ያክል መንገድ ተዘግቶብን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተፈፀመብን ይገኛል። ስለሆነም የአማራ ሕዝብ መብት ተቆርቋሪ አካላትና የግል ሚዲያዎች እንዲህውም የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲያውቅልን ስለመጠየቅ፦ 1ኛ) በጎጃም ቡሬ አቅጣጫ ያለው የትራንስፖርት መንገድ በመንግስት ሀይሎች ዝግ መሆኑ የችግሩን ግዝፈት እንዲጨምር አድርጎታል። 2ኛ) ለሚመለከተው አካል የጉዳታችንን መጠን እንኳን ማሳወቅ እንዳንችል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ኔቶርክ በገዥዎች ትዛዝ መጥፋቱ ገዳይና አስገዳይ ራሱ መንግስት እንደሆነ ይታወቅልን። ወይም ችግሩ እንዲባባስ የመንግስት አካላት አስተዋፆኦ መሆኑ ይሰመርበት። 3ኛ) ለሁለት ዓመት ምስራቅ ወለጋ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ለአማራ ተወላጆች የጤና አገልግሎት እንዳያገኙ ወይም የኦሮሚያ ጤና ተቋማት አግልግሎት እንዳይሰጡን መደረጉ በገዥዎች በኩል እየታወቀ ሰባዊ መብት ተሟጋቾች ዝምታ መምረጣቸው በራሱ የችግሩ ግዝፈት እንዲጨምር ሁኗል። 4ኛ) ምስራቅ ወለጋ ለሁለት ዓመት ምንም አይነት የሸቀጣሸቀጥ ግባቶች እንዳይገቡ ከተደረገ በሆላ የኦሮሚያ ብሔር ተወላጆች የተለያየ ጥቅማጥቅም ወደሚያገኙበት አካባቢ እንዲሂዱ የተደረገ ሲሆን የአማራ ተወላጆች ደግሞ ከተፈፀመብን ብሔር ተኮር ጭፍጨፋ የተረፍነው አማሮች ምንም አይነት የህግ ይሁን የሞራል ከለላ ወይም የእለት ጉርስ እንዳናገኝ ከወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዋች በሀገሪቱ ሰራዊት መንገድ በመዝጋት በሌለኛው አቅጣጫ በኦነግና በኦሮሞ ልዩ ሀይል ከበባ ውስጥ በማስገባት ገዥዎች በወለጋ አማራዎች ላይ ዘር ጭፍጨፋ አወንታዊ ፍቃድ እንዳለው 100% አመላካች ነው። 5ኛ) የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የተሰማራበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው ለብሔር ጭፍጨፋ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ግምባር ቀደም መሆኑ የዓይን ዕማኞች ምስክር መሆናቸው እየታወቀ ገዥዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው መቀመጣቸው የመንግስት እስትራቴጂ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። 6ኛ) የታሰሩ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ከጥር 2 እስከ ጥር 03 /2015 ዓ/ም ድረስ ከነበሩበት አካባቢ ወደ ሌላ የማጓጓዝ ስራ እየሰሩ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን ጥር 3 በመንገድ ላይ እንደነበሩ በፀጥታ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት የእስረኞች ህይወት አልፏል፤ አካል ጎድሏል። ይህ ቀድሞ የተሰራ ፖለቲካዊ አሻጥር መሆኑን አመላካች ነው። እስረኞቹ በጥይት በተመቱበት ወቅት እጃቸው በካቴና፤እግራቸው በእግር ብረት ቁልፍ ካቴና የታሰረ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። 7ኛ) ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ እና አካባቢዋ የአማራ ተወላጆች ከ 200 በላይ በኦሮሚያ ልዩ ሀይልና በመከላከያ ህግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በኦሮሚያ ፀጥታ አካላት እንደተሰወሩ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። 8ኛ) ምስራቅ ወለጋ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሰባዊነት የጎደለው ዘር ጭፍጨፋ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች እንዳይዘግቡትና ዓለም አቀፍ ዜና አቅራቢዎች እንዳይዘግቡት መደረጉ የአማራን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ገዥዎች ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸውን አመላካች ነው። 9ኛ) ለሁለት ዓመት መንገድና ባንክ ለተዘጋበት ሕዝብ እረዴት ሰራተኞች የሰው ህወት አድን እንዳይሰሩ በመንግስት ሀይሎች መከልከሉ ነገር ግን ለኦሮሚያ ብሔር ተወላጆች ደግሞ እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉ እየተካሂደ ያለውን ብሔር ተኮር ጭፍጨፋ መንግስት ዕውቅና የሰጠውና ባለ ዕቅ መሆኑን ማሳያ ነው። ይህ ማለት የወለጋው እልቂት በገዥው አወንታዊ ፍቃድ እየተፈፀመ ያለ መሆኑን የአማራ ሕዝብ መብት ተቆርቋሪ አካላትና የዓለም አቀፍ ሰባዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲያውቅልን እንጠይቃለን!!! ግልባጭ:_ ለ ሳተናው ሚዲያ አማራ ሚዲያ (አሚማ) አሻራ ሚዲያ ፅናት ሚዲያ ሮሐ ሚዲያ ኢትዮ 360 ዘመዴ ነጭ ነጯን መረጃ Tv ንስር ብሮድካስት ጥር 2015 ዓ/ም ከምስራቅ ወለጋ አማራዎች

Source: Link to the Post

Leave a Reply