
በኦሮምኛ ቋንቋ በተለያዩ አካባቢዎች በማገልገል የሚታወቀው መምህር ዓቢይ መኮንን ከእስር ተፈታ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መምህር ዓብይ መኮንን ለጥያቄ እንፈልግሀለን በሚል የጸጥታ ኃይሎች ወስደውት ላለፉት 14 ቀናት በእስር መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በኦሮምኛ ቋንቋ በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በገጠሯ ቤተ ክርስቲያን በማገልገል የሚታወቀው መምህር ዐብይ መኮንን ለጥያቄ እንፈልግሀለን በሚል የጸጥታ ኃይሎች ወስደውት ላለፉት 14 ቀናት በእስር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር መፈታቱ ታውቋል፡፡ ኢትዮ መረጃ ኒውስ እንዳጋራው።
Source: Link to the Post