በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ ድብደባና ማሰቃየት እንዲሁም ሕገ-ወጥ እስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው እጅግ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብ…

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ ድብደባና ማሰቃየት እንዲሁም ሕገ-ወጥ እስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው እጅግ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብ…

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ ድብደባና ማሰቃየት እንዲሁም ሕገ-ወጥ እስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው እጅግ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ ዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ በኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ ድብደባና ማሰቃየት እንዲሁም ሕገ-ወጥ እስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው እጅግ እንዳሳሰበው ገልጾ የሰዎች ደህንነት እና ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ ሲል ጠይቋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ ከአሁን ቀድም በኦሮሚያ ክልል፣ በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ውስጥ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና መንግሥት ሕጋዊ፣ ትክክለኛና ተገቢ የሆኑ የመፍትሔ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥቅምት 21 እና 24 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣቸው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ማሳሰቡን አውስቷል። ሆኖም፣ በእነዚህ አካባቢዎች ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና በሰዎች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን፤ ኢሰመጉ በየሳምንቱ ከሚያከናውነው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ዳሰሳ ለመረዳት ችሏል ነው ያለው፡፡ ኢትዮጵያ ፈርማ ያጸደቀቻቸውና የሕጎቿ አካል ያደረገቻቸው ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች ሰዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ፣ በማንኛውም ቦታ በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብቶች እንዳሏቸው ይደነግጋሉ ሲል ጠቅሷል፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ- መንግሥትም ማንኛውም ሰው ‹ሰው› በመሆኑ ብቻ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት እንዳለው በአንቀጽ 14 ሥር ስለመደንገጉም ገልጧል፡፡ ይሁንና፣ በኦሮምያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ስር ባሉ አካባቢዎች ጸጥታ አስካበሪዎችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች በሕይወት የመኖር መሠረታዊ መብታቸው ታጣቂ ኃይሎች እንዲሁም የክልሉ መደበኛ ፖሊስ እና ልዩ ኃይል አባላት በሚወስዱት እርምጃ እየተጣሰ፣ ከፍርድ ውጪ ተገድለዋል ሲል ነው ኢሰመጉ የሁኔታውን አሳሳቢነት የገለፀው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply