በኦስሎ፣ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ታላቅ ሰልፍ አደርጉ። የሰልፉን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶዎች፣ለኖርዌይ ሕዝብ የተበተነው ወረቀት ፅሁፍ እና ሰልፉን የሚያሳይ ሙሉ ቪድዮ ሊንክ ያግኙ።

በሰልፉ ላይ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ተሳትፈዋል።የሰልፉ ዓላማ የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት፣የሐሰት ዜና ማሰራጫዎች እና የሽብርተኛው ህወሓት እና ኦነግ ሸኔን በማውገዝ ነበር።በሺህ የሚቆጠር የኢትዮጵያን እውነተኛ ገፅታ የሚገልጥ ወረቀት እና ሊንክ ኮድ በኦስሎ ለሚኖሩ የኖርዌይ ዜጎች ታድሏል።ሰልፉ በመሃል ከተማ መፈክሮች እያሰማ በኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኖርዌይ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኤን አር ኮ) ፊት ለፊት ተሰልፏል።በሰልፉ ላይ የቀድሞው የህወሓት መስራች ህወሓትን በማውገዝ ንግግር አድርገዋል።የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኮሚኒት እንዲሁም የሲቪክ ድርጅቶች ተወካዮች ንግግር አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply