በኦነግና ትህነጋዊን መሃል ተከቦ አማራ ነኝ ማለት ዘመኑ የጠየቀው ብርቱ አቋም ነው! አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 21 /2013 ዓም ባህር ዳር የአማራ ህዝብ አሁን…

በኦነግና ትህነጋዊን መሃል ተከቦ አማራ ነኝ ማለት ዘመኑ የጠየቀው ብርቱ አቋም ነው! አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 21 /2013 ዓም ባህር ዳር የአማራ ህዝብ አሁን ባለንበት ዘመን ዓለም የደረሰችበትን መንግስታዊ ፤ተቋማዊ፤ ግለሰባዊና ሙያዊ ስኬት እንዲሁም ሌሎች ተግባራት ሁሉ አብሮ የሚጓዝ ብቻ ሳይሆን መስራችና ባለቤት ስለመሆኑ አማራን ለማጥፋት ሌት ከቀን የሚታትሩ ሁሉ የሚያውቁት እውነታ ነው፡፡ የአማራ ህዝብ በየጊዜው የሚመጡ ብሄራዊ ፈተናዎችን እንዴት መወጣት እንዳለበት መላ በመምታት፤ዘዴ በመዘየድ፤የሚወዳደረው እንደሌለ ታሪክ ያስረዳል፡፡ታግሎ የሚጥል ስለመሆኑም እንዲሁ…… የአማራ ህዝብ ሰላም ወዳድ ነው ማለት ‘’ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራው ይምከረው’’ በሚለው ብሂል መክሮና ዘክሮ ፤ተበድሎ በትዕግስት ቻል ያደርጋል ፤ጊዜ ይሰጣል ማለት እንጅ የአማራ ህዝብ ጦርነትም ሆነ መግደል አይወድም ማለት አይደለም ፡፡ ይ ወ ዳ ል ፡፡ ዛሬ ላይ በአማራ ህዝብ ዘንድ የተደቀኑ ፈተናዎች የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ከሚደረጉ ዘመቻዎች ውስጥ ውስጥ ይመደብ እንጅ የአማራ ህዝብ አይጠፋም፡፡ በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያ ለአማራ ህዝብ ሞቶ የሚወርሳት ገነቱ አይደለችም የሚለው አባበቃል ለሰማይ ለምድር የከበደ ጊዜው የሚዋጀው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ምክንቱም ኢትዮጵያን ሀገር አድርጎ ባቆየ ፤መጥፎ ሳይሆን ዘመን የማይሽረውን በአለም አደባባ በኩራት ከፍ ብሎ ዛሬም ዘወትርም የሚያኮራ ታሪካዊ አሻራን በመስራት የዚህች ሀገር የክብር ህዝብ እንጅ በወራሪ እየጠገደለ ነገን ተስፋ በማድረግ ከወሬ በዘለለ አንዳችም መፍትሄ በሌለው መንግስታዊና ግለሰባዊ የውስጥ አባሪ ተባባሪነት በጽንፈኞች መገደልና መሳደድ የለበትም፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል አንድ ሁለት ብለን እንቁጠር ብንል የዳታ ቤዝ ማሽን ወይም የግፍ መመዝገቢያ መሳሪያ ሊያስፈልገን ይችል ይሆናል እንጅ ከባለ ስልጣን እስከ ንጹሀን ግድያ፤ ከርስት እስከ ሀብት ዘረፋ፤ ከማሳደድ እስከ ማሳበድ ያልተገባ ኢ ሰብዓዊና ዘመን አመጣሽ የጠረኞች ግፍ የለም፡፡ የአማራ ህዝብ ትናንት ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ከሚጠራው ሀይል ጋር እየሞተ ታግሎ ህወሓትን ላትመለስ የሸኘው ዛሬ ኦሮሞን ለመገንጠል ሌት ተቀን በሚታትረው የኦነጋዊያን ሀይሎች ለመሞት አይደለም ፡፡ ይህ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ፤ ባሌ ጎባ ፤ባሌ ሮቤ እና ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ከግድያ ተርፈው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ወደ አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የገቡ ንጹ ሀን አማራዎች አይደለም ያጡትን የሰው ህይወት የሚያጽናና ፤የስነ ልቦናና የሀብት ካሳ ይቅርና ተገቢውን የሆነ የቀን ጉርስ የሌት ልብስ እንኳን ሳያገኙ በችግር ውስጥ ናቸው ፡፡ ግድያው ቀጠለ… በመተከል በሽዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በክስታቸው ድረስ በጠብ መንጃ ፤በቀስትና በስለታም ነገር አይሆኑ ሆነው ተገደሉ፡፡ ከሞት የተረፉት ተሳደዱ፡፡ አሁንም ችግር ውስጥ ስለመሆናቸው ይናገራሉ፡፡ መንግስት ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሄ ሳይሰጥ በቤንች ሸኮ የተደራጁ የመንግስት ባለስልጣናት የብሄሩን ተወላጆች በማስተባበር በሌሊት ሀገር ሰላም ብለው በተኙበት ታረዱ፡፡ አሁንም መልስ የለም፡፡???? በምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለሳምንታት በቀጠለው አማራን የመግደል ዘመቻ በጫካ የታረዱ ስለመኖራቸውና አሁንም ዳብዛቸው የጠፉ እንዳሉ የአይን እማኞች ይናገራሉ፡፡ ከግድያ ተርፈው ወደ አማራ ክልል የገቡትም ቢሆን እስካሁን ድረስ እንደቀጠለ ሲሆን በሽዎች የሚቆጠሩ ለከፋ ችግር እንደተዳረጉ እየጠናገሩ ይገኛል፡፡ የአማራን ህዝብ ሰላማዊ ህይወት ለማስቀጠል አማራው እንደ አማራ መደራጀት አለበት የሚለው ዘመን የማይሽረው ብሂል ቀድመው የገባቸው ምሁራንና ሊቃውንት ከግራም ከቀኝም ወከባ በዝቶባቸው ሳይጠቅሙን ሲያልፉ ከጠላት መትረጊስ የተረፉት ደግሞ የሚያደርጉት ጠፍቶባቸው ቤታቸው ይገኛሉ፡፡ የአማራ ህዝብም ሲገደል፤ሲሳደድ ፤ሲታረዝ እየጠመለከቱ ነው፡፡ ምክንያቱም አማራ እየሞተ ነው ቢሉ የሚከተላቸውን ያውቁታል፡፡ ለዘመናት በጠላት እጅ ወድቆ እንደ ምስጥ በሚቦረቡሩ ሀይሎች ህሎናውን ለመናድ የሚደረገው የዘወትር ጥረት መቆም አለበት፡፡ በዚህ አጋጣሚ በሽዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከዕለት ምግብና መጠለያ እስከ ዘላቂ ሰላምና የህይወት ዋስትና ድረስ ድጋፍ ስለሚያስፈልጋቸው የዚህ ጊዜ ነው ወገን አለሁ የሚል እንላለን፡፡ አዘጋጅና አቅራቢ፡- ማርሸት ጽሀው https://youtu.be/kBdOcmrALQU

Source: Link to the Post

Leave a Reply