በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የውሃ ችግር እንደገጠማቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በህዝብ ተዋካዮች ምክርቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ወደ ከተማዋ የሚገባውን የውሃ መስመር በመቆጣጠሩ የውሃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።
አሁንም ድረስ የቡድኑ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌዎችን ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሰምተናል።
የጉንዶ መስቀል ከተማን ይመግ የነበረው የሃገዩ የውሃ መስመር በመቋረጡ ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች ንፁህ መጠጥ ውሃ እያገኙ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በዚህም ምክንያት የጉድጓድ ውሃ ለመፈለግ የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል።
ከውሃ ችግሩ ባለፈም የከተማዋ ነዋሪዎች የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በወረደዋ በርካታ የገጠር ቀበሌዎችን ታጣቂዎቹ በመቆጣጠራቸው የሰብል ማሰባሰብ ስራውን እንዳስተጓጎሉ ተነስቷል።
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 08 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post