በኦዴፓ ብልፅግና፣ ያደገው ምርት ሳይሆን፣ የዋጋ ንረት ነው! ህዝብ ከዳቦ ጥያቄ ወደ መኖር ጥያቄ ተሸጋገረ! ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

በዘመነ ብልፅግና ፓርቲ በገበታ ለልማት ኢኮኖሚ ህዝብ በኑሮ ውድነት በማያባራ የዋጋ ግሽበት ተመታ!

‹‹መንግሥትና ዝናብ ከላይ፣ ምስጥ ከታች ነው የሚመጣ!!!›› የጠገዴ ወረዳ፣ የማክስኞ ገበያ ገበሬ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ እንደ ሚልተን ፍሪድማን ‹‹የዋጋ ግሽበት ማለት ያለ ሕግ አውጭ የተጣለብን ተጨማሪ የግብር አከፋፈል ነው፡፡›› Inflation is taxation without legislation. Milton Friedman

በኦዴፓ ብልፅግና፣ ያደገው ምርት ሳይሆን፣ የዋጋ ንረት ነው!!! ህዝብ ከዳቦ ጥያቄ ወደ በህይወት የመኖር ጥያቄ ተሸጋገረ!!!  ‹‹ለምን ኬክ አይበሉም!!!›› ………..‹‹ዳቦ ብቻ…ጁስ የለም!!!›› ዶክተር አብይ አህመድ

 • በየካቲት ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት6 በመቶ መድረሱን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ባለፉት ስድስት ወራት ከተመዘገቡት ውስጥ በጣም ትልቁ ሲሆን፣ ጭማሪው ምርቶች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ ያሳዩት ለውጥ ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል። በተመሳሳይ የምግብ ዋጋ ግሽበት 22.8 በመቶ ሲደርስ፣ ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ 18 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ መታየቱን ኤጀንሲው አስታውቋል።
 • የማዕከላዊ ስታስቲክስ ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በትግራይ ክልል ሲሆን6 በመቶ ደርሷል። አነስተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት በመሆን የተመዘገበው በአማራ ክልል (14.1 በመቶ) እንደሆነ የገለጸው ሪፖርቱ፣ በአዲስ አበባ ደግሞ 25.7 በመቶ መድረሱን አመላክቷል።

በተለይም መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ካደረገ ጊዜ አንስቶ ሁሉም የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። ለአብነት በአዲስ አበባ በአንድ ወራት ውስጥ ብቻ የታየውን ግሽበት ማንሳት ይቻላል። ከሁሉም ምግቦች በላይ ተፈላጊ የሆነው ጤፍ በኩንታል ከ4,300 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ ሲል የስንዴ ዱቄት ዋጋ በእጥፍ ጨምሮ 4,000 ብር ሊገባ ችሏል።በተመሳሳይ የአምስት ሊትር ዘይት ዋጋ ከ360 ብር ወደ 470 ብር የጨመረ ሲሆን፣ የእንቁላል ዋጋ ከአምስት ብር ወደ ሰባት ብር ከፍ ብሏል። ለሁሉም ጭማሪዎች እንደ አንድ ምክንያት ተደርጎ የሚወሳው የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ 20 በመቶ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎችም ከ30 እስከ 50 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ማስተካከያ አድርገዋል። በአዲስ አበባ የምግብ ምርቶች ዋጋ ዳቦ ትንሾ ከ3ብር እስከ 3.50፣ እንጀራ 7 ብር፣  ሎሚ ከ4ብር እስከ 5 ብር ፣ ድንች ኪሎ 15 እስከ 20 ብር፣ ቲማቲም ኪሎ 17 እስከ 25 ብር፣ ሽንኩርት ኪሎ ከ15 እስከ 20 ብር፣ ቅቤ ኪሎ ከ300 እስከ 450 ብር፣ ሥጋ በኪሎ ከ300 እስከ 400 ብር፣ አጃ 130 ብር፣ ሾላ ወተት 17 ብር፣ ነጭ ጤፍ ከ4600 እስከ 5000 ብር፣ ሠርገኛ ጤፍ ከ4300 እስከ 4500 ብር፣ ቀይ ጤፍ ከ4200 እስከ 4400 ብር፣ በቆሎ ከ1900 እስከ 2000 ብር፣ ስንዴ ከ2800 እስከ 3000 ብር በኩንታል እየተሸጡ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ነው  በኦዴፓ ብልፅግና፣ ያደገው ምርት ሳይሆን፣ የዋጋ ንረት ነው! ህዝብ ከዳቦ ጥያቄ ወደ በህይወት የመኖር ጥያቄ የተሸጋገረው፡፡ መጀመሪያ አውደ ኢኮኖሚው በህግና ሥርዓት መመራት አለበት፡፡

 • በኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚወጣባቸውና መሠረታዊ ከሚባሉ ምርቶች መካከል የምግብ ዘይት አንዱ ነው፡፡ በዓመት ከ620 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማለትም ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበትም ነው፡፡
 • ኢትዮጵያ በየወሩ 52 ሚሊዮን ዶላር ለምግብ ዘይት ፍጆታዋ ወጪ ታደርጋለች፡፡ በዚህ መረጃ ሥሌት መሠረት በየወሩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የምግብ ዘይት ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን፣ በግብይት ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው መሠረታዊ የሆኑ ፍጆታ ምርቶች አንዱ ያደርገዋል፡፡ ከፍተኛ ወጪ የሚደረግበት የምግብ ዘይት ግን በገበያ ውስጥ በተደጋጋሚ እጥረት ያለበትና ሸማቹ እጅ እንደተፈለገ የማይገባ ነው፡፡

የዋጋ ግሽበትና ሸማቹ ደሃ ህብረተሰብ፣በተለይ በአብዛኛው ከምግብ ጋር በተያያዘ የዋጋ ግሽበቱ 47 በመቶ በሸማቹ ህብረተሰብ ላይ መሆኑን ገልጸው እንደቀላል ነገር የብሄራዊ ባንክ ገዝው አጣጥለውት አልፈዋል፣ ኢትዩጵያ ከባህር ማዶ ወደ ሃገር ውስጥ ከምታስገባቸው የምግብ ፍጆታ ሸቀጣ ሸቀጦች በአስመጪው ነጋዴ ወደ ሃገር ውስጥ ባስገባቸው ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ የተከመረው  የትርፍ ህዳግ ዞሮ ዞሮ ሸማቹን ህብረተሰብ እንደሚጎዳው የኑሮ ውድነቱም በተለይ በምግብ ፍጆታ እቃዎች ለምሳሌ በዘይት፣ በዱቄት፣ ወዘተ አላቂ እቃዎች ሸማች ህብረተሰብ ላይ የባሰ እንደሆነ ግልፅ ሆኖ ሳለ  እንደቀላል የሚያልፉት ስለምን ይሆን፣ ነጋዴዎች ብዙ ትርፍ በማግበስበስ ዳግም ወደ ባንክ ይወስዳሉ፡፡ ባንኩ እንደገና ለነጋዴዎች ያበድረዋል፡፡ ነጋዴዎች በዚህ መንገድ ስለሚሰራ ይተረፋል፡፡ ከባንክ ወደ ብድር፣ ከብድር ክፍያ ወደ ባንክ እያለ ገንዘቡ ይሽከረከራል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ በሸማቹ ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ተፅፅኖ የዋጋ ግሽበት እየፈጠረ እያለ ነጋዴው በፈለገው የትርፍ ህዳግ ያላመረተውን ሸቀጣ ሸቀጥ በመሸጥ ይከብራል፡፡ በህብረተሰቡ በኑሮ ውድነት ማለትም በከፍተኛ የዋጋ ግሸበት ይሰቃያል፡፡ በእኛ አገር የዋጋ የግሽበት ቅርጫትዋ በአብዛኛው ከምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ ጋር የተያያዘች ስለሆነች የከተማው ህብረተሰቡ ከገቢው 55 በመቶ ወጪ በማውጣት፣ የገጠሩ ህብረተሰብ 65 በመቶ ከገቢው ወጪ በመክፈል  ይሰቃያል፡፡ የዋጋ ግሽበቱ አካል የሆነው ምግብ 47 በመቶ ነው የሚይዘው፡፡ ህብረተሰቡ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ ንግድ በዚህ መልክ ይበዘበዛል፡፡ ሸቀጣ ሸቀጥ ከውጭ አስመጥተው በመሸጥ የሚተዳደሩት ፍቃድ የተሠጣቸው ኢምፖርት ፍቃድ ያላቸው ነጋዴዎችና የኢህአዴግና የብልጽግና አስመጭና ላኪ ድርጅቶች በመሆናቸው የትርፍ ህዳግ ማንም አያደርግባቸውም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ 90 በመቶ መኪናዎች ከውጭ እያስመጡ የሚሸጡ እነርሱ ናቸው፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ በኑሮ ውድነት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጠቂ ሆኖል፡፡

የዋጋ ግሽበት/ የዋጋ ንረት፡- የአንድ አገር የገንዘብ እሴት  መርከስ የመግዛት አቅም መቀነስ ቀስ በቀስ በጊዜ ሂደት ውስጥ ይከተላል፡፡ በምርትና ሸቀጦች አጠቃላይ ዋጋ መጨመር በመቶኛ ሲሰላ የገንዘብ የመግዛት አቅም በፊት ከነበረበት የመቀነስ ሂደት ነው፡፡ የዋጋ ግሽበት፡- የአንድ አገር የገንዘብ እሴት  መርከስ በዚህም የተነሳ በኢኮኖሚው ውስጥ አጠቃላይ የምርቶች፣ ሸቀጦችና አገልግሎቶች  ዋጋ መጨመር ነው፡፡ የዋጋ ግሽበት የሚለካው  በኢኮኖሚው ውስጥ የምርቶች፣ ሸቀጦችና አገልግሎቶች  ዋጋ መጨመር ነው፡፡ የዋጋ ግሽበት የሚፈጠረው  የምርቶች ዋጋ መጨመር ማለትም የጥሬ እቃዎች ግብአት ዋጋ መጨመር እንዲሁም የሠራተኞች የጉልበት ዋጋ ደሞዝ መጨመር ይከሰታል፡፡ የሸማቾች ምርት፣ ሸቀጦችና አገልግሎት  የመግዛት ፍላጎት መጨመር የዋጋ ንረት ያስከትላል፡፡ ሸማቾች ምርቱና ሸቀጦች ከፍ ባለ ዋጋ ለመግዛት ፍቃደኞ መሆኑን ያሳያል፡፡ የዋጋ ግሽበት ወይም የዋጋ ንረት ምሳሌ በ1913 እኤአ የአንድ ጋሎን ወተት ዋጋ ሠላሳ ስድስት ሣንቲም በጋሎን ነበር፡፡በ2013 እኤአ ከመቶ አመታት በኃላ የአንድ ጋሎን ወተት ዋጋ ሦስት ብር ከሃምሳ ሦስት ሆነ፡፡ በግምት አሥር እጥፍ ነበር ያደገው፡፡ ይሄ ጭማሪ የተከሠተው ወተት አቅርቦት ማነስ ወይም ለማምረት ውድ በመሆኑ ምክንያት አልነበረም፣እውነቱ በተቃራኒው የሆነው ነው፡፡ 
የዋጋ ንረት፡ በጎ ጎን ውስጥ የሸማቾች የመግዛት ፍላጎት መጨመር የተነሳ የመብል ፍጆታ እቃዎች ምርትና ሸቀጦች አቅርቦት መጨመር የኢኮኖሚ እድገት አንቀሳቃሽ ኃይል ይፈጥራል፡፡

በዓለማችን ማዕከላዊ ባንኮች የተረጋጋና ተመጣጣኝ የዋጋ ንረት አሊያም የዋጋ ግሽበት ኢላማ ከ2 እስከ 3 በመቶ በዓመት ነው፡፡ (Most of the world’s central banks target modest levels of inflation, at around 2%–3% per year.) ከፍተኛ የዋጋ ንረት የአንድ አገርና ኢኮኖሚ ይጎዳል፣ የሸቀጦችና ምርቶች ዋጋ በአፋጣኝ መጨመርን ያስከትላል፣ አንዳንዴ ከሠራተኛ ደሞዝ ጭማሪ በላይ የሸቀጦች ዋጋ ይጨምራል፣ ብሎም የኑሮ ውድነት ይከሠታል፡፡

 

የዋጋ ግሽበት ወይም የዋጋ ንረት ከ2020 እስከ 2021እኤአ/Ethiopia Inflation Rate2020-2021 Data| እንደ ኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ቢሮ መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ አመታዊ የዋጋ ንረት ከ 19.2 በመቶ በጀንዋሪ፣ 20.6 በመቶ በፌብርዋሪ 2021 መድረሱን ያሳያል፡፡ የምግብ ዋጋ ፍጆታ፣ የኮሮና ቨይረስ በሽታ ወረርሽኝ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የአንበጣ ወረርሽን፣ የቤንዚን ዋጋ መጨመር፣ የቤት ኪራይ መጨመር፣ ወዘተ ያሳያል፡፡ በአዲስ አበባ  ከተማ ሠራተኛ ህዝብ የምግብ ነክ ወጪ ከ54 በመቶ እስከ 60 በመቶ ይደርሳል፡፡ ቀሪው ወጪ ለቤት ኪራይና ለአልባሳት  የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይ ወጪ ከምግብ ነክ ወጪ ጋር ሲወዳደር እኩል ካለዛም ሊበልጥ ይችላል እንላለን፡፡ የኮንስትራክሽን ነክ ወጪም የሲሚንቶ፣ የብረት፣ወዘተ ዋጋም ከፍተኛ ሆኖል፡፡

የመንግሥትና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶቸ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እዳ መጨመር፣ አመታዊ የእዳ ወለድ የመክፈል አቅም ማጣፍያው ማጠር፣ የመንግሥታዊው ዘርፎች ወጪ መጨመር፣ የግብርና ታክስ መሰብስብ ችሎታ ዝቅተኛነት፣ መርምረን ሳንጨርስ የአስር አመት እቅድ ነድፈን ሳንተገብር፣ ሃገሪቱ በምርጫ እየታመሰች ሳለ ዳግም  ሃገሪቱ በጦርነት ኢኮኖሚ ተዘፈቀች፡፡

 

 

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መንግሥትና ብሄራዊ ባንክ የሃገሪቱን ሞኒተሪ ፖሊሲ፤ (Monetary Policy) በመንደፍ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ የገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሥርዓት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤የገቢ ፖሊስ፣ የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት  በፍጆታ እቃዎች ላይ እድገቱን ለማሳየት (Development of inflation rates for consumer goods in Ethiopia) በ2015 (9.57%)፣ በ2016 (6.63%), በ2017 (10.68%), በ2018 (13.83%), በ2019 (15.84%), በ2020 (22.6%) በ2021 (20.6%) በዓለማችን ማዕከላዊ ባንኮች የተረጋጋና ተመጣጣኝ የዋጋ ንረት  ከ2 እስከ 3 በመቶ በዓመት ይገመታል፡፡  በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት  በፍጆታ እቃዎች ላይ ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ -9.8 በመቶ እስከ 44.4 በመቶ ተስተውሎል፡፡ በ2019 እኤአ 15.8 በመቶ የዋጋ ንረት ተከስቶ ነበር፡፡ ከ1979 እስከ 2019 እኤአ አመታት ውስጥ አማካይ የዋጋ ንረት 9.4 በመቶ በዓመት ነበር፡፡ በአጠቃላይ የእቃዎች ዋጋ በ2892.12 በመቶ ጨምሮ ነበር፡፡ ያም ማለት በ1979 እኤአ መቶ ብር ያወጣ የነበረ እቃ በ2020 መጀመሪያ ወር ላይ 2992.12 ብር ዋጋ እድገት አሳይቶል፡፡ በ1979 መቶ ብር የተሸጠ በግ በ2020 እኤአ 2992.12 ብር ተሸጠ እንደማለት ነው፡፡

“Development of inflation rates in Ethiopia:- The inflation rate for consumer prices in Ethiopia moved over the past 40 years between -9.8 % and 44.4 %. For 2019, an inflation rate of 15.8 % was calculated. During the observation period from 1979 to 2019, the average inflation rate was 9.4 % per year. Overall, the price increase was 2,892.12 %. An item that cost 100 Birr in 1979 was so charged 2,992.12 Birr in the beginning of 2020.” (1)

ከደንበኞች ከተሠበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፈለው ወለድ ከዋጋ ንረት በላይ መሆን አለበት!!!

የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የባንክ ቅርንጫፎች ከ680 ወደ 3900 አድገዋል፤ከፍተኛ የቁጠባ ገንዘብ ማሰባሰብም ተችሎል ብለዋል፡፡ ከምርት ዕድገት ጋር ባልተጣጣመ መንገድ፤ ገንዘብ ኢኮኖሚው ውስጥ ለሚረጨው ጥሬ ገንዘብ ምንጮቹ ብሔራዊ ባንክ እንዲሁም በመንግሥት ትዕዛዝ ጭምር በገፍ የሚያበድረው የኢትዩጵያ ንግድ ባንኮች ናቸው፡፡ መንግስታዊ ልማት ድርጅቶች ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ  780 ቢሊዮን ብር ብድር ተበድረው መክፈል አልቻሉም፡፡ በተለይ እነዚህ ሁለት ባንኮች ኢኮኖሚው ውስጥ በሚያንቀሳቅሱት ገንዘብ ምክንያት የዋጋ ንረት እየጨመረ መጥቶል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) በ2010ዓ/ም 2.2 ትሪሊዮን ብር፣ በ2011ዓ/ም 2.7 ትሪሊዮን ብር፣ በ 2012 ዓ/ም 3.375 ትሪሊዮን ብር ወይም 107.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በጊዜው ዋጋ ከነበረበት 60 ቢሊዩን ብር ገደማ፣ በአሁኑ ጊዜ ከ3.4  ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልፆል፡፡ በግልፅ ለማስቀመጥ ያደገው ምርት ሳይሆን፣ የዋጋ ንረት ነው፡፡  ኢኮኖሚው አንዴ አስር በመቶ አንዴ 11 በመቶ አደገ ቢባልም፣ በሃገሪቱ ጠቀላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ማለትም የግብርና ምርቶች፣ የፋብሪካዎች ሽቀጣ ሸቀጦችና፣ የአገልግሎትና ምርቶች እድገት ሳይሆን የዋጋ ንረት ነው ያደገው፡፡

ድሮ አንድ እንቁላል አምስት ሳንቲም ቢሸጥ ዛሬ 7 ብር 75 ሣንቲም ይሸጣል፡፡ ድሮ አንድ ሎሚ አምስት ሣንቲም ሲሸጥ ዛሬ ከ 3 እስከ 4 ብር ይሸጣል፡፡ የፍጆታ ዕቃዎች   የጤፍ፣ የዱቄት፣ ዘይት ወዘተ ዋጋ መናር የእለት ተእለት ክስተት ነው፡፡ ኢኮኖሚው አደገ ከተባለ ምርት በሽበሽ ይሆናል ዋጋቸው ይቀንሳል፡፡ የምርት አቅርቦት ሲጨምር፣ ፍላጎት ይቀንሳል፣ ዋጋቸውም ይቀንሳል፡፡ በተቃራኒው  የምርት አቅርቦት ሲቀንስ፣ ፍላጎት ይጨምራል፣ ዋጋቸውም ይጨምራል የሚል የምጣኔ ኃብት መርህ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ውስጥ ግን አልሰራ አለ፡፡ ሰው በተዓምር ነው የሚኖረው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  ሸቀጣ ሸቀጥ ከውጭ አስመጥተው በመሸጥ የሚተዳደሩት ፍቃድ የተሠጣቸው ኢምፖርት ፍቃድ ያላቸው ነጋዴዎችና የኢህአዴግና የብልጽግና አስመጭና ላኪ ድርጅቶች ከባህር ማዶ ባስመጡት ሽቀጣ ሸቀጦች ላይ አስራ አምስት በመቶ የትርፍ ህዳግ ጨምረው እንዲሸጡ መቆጣጠር የብሔራዊ ባንክ ስራ ሆኖ ሳለ ነጋዴዎች በፈለጋቸው ዋጋ እንዲሸጡ ዝም በማለት ተባባሪ ሆኖ ህዝብ ሲያዘርፍ አመታት ተቆጥሮል፡፡ ባንኩ የዋጋ ንረትና መቆጣጠር አልቻለም የወደፊትም እቅድ አይታይም፡፡  በያመቱ የሚታየው የዋጋ ለውጥ ከፍተኛ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋጋት ላይ በቁጥጥር ስለሆነ እንጂ ኢኮኖሚው የመግዛት አቅሙን ዝቅተኛነት እያጋለጠበት በመሆኑ የብሄራዊ ባንኩን ውጤት ዝቅተኛ ያደርግበታል፡፡ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትም ቢሆን የሚያኩራራ አይደለም፡፡ የመንግሥት ኢንቨስትመንት በተለይ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች 780 ቢሊዮን ብር እዳ ድርጅቶቹ አምራቾች ሳይሆኑ የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ አድርገዋል፡፡ የግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ አንደኛ የሥራ ዕድል ማመንጨት እንዳይችል መደረጉ ሁለተኛ የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት አለመቻሉ ሦስተኛ አገራዊ እዳ መቆለሉ የሃገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዳይረጋጋ አድርጎል፡፡ የሃገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚን ለማረጋጋት የግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ  ሥራ ፈጠራ የሥራ ዕድል ማመንጨት ማመቻቸት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር፣ የውጭ ንግድ ገቢን ማጠናከር፣ የመንግሥት ወጪን መቀነስ፣ የአገር ውስጥ ገቢን ማሻሻል ግብርና ታክስ አሰበባሰብን ማዘመን፣  የውጭ ምንዛሪ እጥረትን መቅረፍ፣ የመዋቅር ማስተካከያ መድረግ ያሻል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተፅዕኖ ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ተመን በገበያ ኢኮኖሚ እንዲወሰን በማስገደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የአንድ ዶላር ዋጋ ተመን በነፃ ገበያ በጥቁር ገበያ ከተወሰነ የዋጋ ንረቱ ይበልጥ ይባባሳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብዙ ገንዘብ እንዲታተም በማድረግ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚንቀሳቀስ የገንዘብ መጠን በባለፈው አስራ አምስት አመታት ውስጥ ወደ 900 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ተሰራጭቶል፡፡ የብር ህትመት  የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ በማድረግ እንዲሁም ገንዘቡ የዋለበት መንገድም ትክክለኛ ባለመሆኑ፣ ሙስናና የኃብት ብክነት እንዲስፋፋ ምክንያት እንደሆነ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አሳስበው ነበር፡፡

ከደንበኞች ከተሠበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፈለው ወለድ ከዋጋ ንረት በላይ መሆን አለበት!!!

የካቲት 22 ቀን 2009 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹‹ በኢትዩጵያ ባንኮች የሚከፍሉት የወለድ ምጣኔ ከዋጋ ግሽበት መጠን አነስተኛ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ የወለድ መጠን አምስት በመቶ ሲሆን የዋጋ ግሽበት መጠኑ በአማካይ 7 እስከ 9 በመቶ ደርሶል፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ የባንክ ደንበኛ ገንዘቡን በባንክ ሲያስቀምጥ ወለዱ ከግሽበቱ ያነሰ በመሆኑ የሚያገኘው ወለድ በግሽቱ ይወሰድበታል ማለት ነው፡፡  በዚህ የተነሳ አንድ ሰው ገንዘቡን ባንክ የሚያስቀምጠው ወለድ አገኛለሁ ብሎ ሳይሆን ሌባ እንዳይሰርቅብኝ ብሎ በመስጋቱ ነው ወደሚል ድምዳሜ እንደሚያደርስ የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ምሁራኑ የወለድ ምጣኔ ከግሽበት ማነስ የለበትም ባይ ናቸው፡፡ በተለይ የቁጠባ መጠንን ለማሳዳግ የባንኮች የወለድ መጠን ከግሽበቱ በላይ መሆን አለበት የሚለው የኢኮኖሚ ምሁራን ምክረ ሃሳብ ነው፡፡›› (2)

 • ‹‹ በአገራችን ግሽበቱ በአማካይ ከ8 እሰከ 10 በመቶ መካከል ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የወለድ ምጣኔው አምስት በመቶ ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ልዩነት በመኖሩ ሰው ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመት ይልቅ የተለያዩ ንብረቶችን (መሬት፣ ቤት፣ መኪና) ግዥ ላይ ሲያውለው ይታያል፡፡ ምክንቱም የቤትና መሰል ንብረቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ስለሆነ በእነዚህ ንብረቶች ላይ ገንዘቡን ማፍሰሱ ግሽበቱን ይከላከልለታል፤ብሩም የመግዛት አቅም ዋጋ እንዳያጣ ያደርግለታል፡፡… ወለድ ከግሽበት በታች መሆኑ ቁጠባን አይጎዳም የሚለው በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ ሌሎች ጉዳዩችም አሉት፡፡ ለምሳሌ በኢትዩጵያ ትልቅ ግሽበት ያለው ንብረት ላይ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የቤት ዋጋ በየግዜው እያሻቀበ ነው፡፡ ስለዚህ ባለገንዘቡ ብዙ ጊዜ ገንዘቡን ግሽበቱን ሊያሸንፍ በሚችልበት መልኩ ሊያውለው ይችላል፡፡ ይህም በዓይነት የተደረገ ቁጠባ ነው፡፡…. በአንጻሩ ከባንክ ብድር የሚወስድ ሰው ይጠቀማል፡፡ ምክንያቱም ንብረት ላይ በማዋል የገንዘቡን የመግዛት ዋጋ ከፍ ማድረግ ይችላልና፡፡ ለምሳሌ ቤት ገዝቶ የሚያከራይ ሰው የቤት ኪራዩን ከፍ በማድረግ ሊጠቀም ይችልል፡፡ ንብረት የሚሸጡ ሰዎችም ከግሽበቱ እኩል ወይም በላይ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን ይችልሉ፡፡…. ገበያው ግሽበት በሚያመጣ ፖሊሲ ላይ የተቀመጠ ከሆነ ግሽበቱ መምጣቱ አይቀርም ፡፡ ስለዚህ የመንግሥት ኃላፊነት ግሽበቱ መስመር እንዲይዝና ወደ ታች እንዲወርድ ማድረግ ይሆናል፡፡››
 • የዋጋ ግሽበት – ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ = ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ — ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • Inflation rate % – Saving rate % = saver are losing _ birr  on each 100 birr saved
 • በ2007አኤአ የዋጋ ግሽበት9 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 11.9 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 11.9 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • በ2008እኤአ የዋጋ ግሽበት0 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 25.0 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 25 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • በ2009እኤአ የዋጋ ግሽበት0 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 18.0 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 18 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡

ከመጋቢት 2010 አስከ መጋቢት 2013 ዓ/ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አስተዳደር

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ መጋቢት ወር 2010 ዓ/ም የአንድ ዶላር መገበያያ ዋጋ 27 ብር ከ87 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፣  መጋቢት 2013ዓ/ም 41 ብር ደርሷል። የብር ዋጋ ከዶላር አንፃር በ47.1 በመቶ እንዲዳከም ተደርጓል። አገሪቱ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ በመሆኗ የምንዛሪ ዋጋ ማስተካከያው የዕቃዎችን ዋጋ እንዳስወደደ ተናግረዋል። በዚህ መጠን ብር መዳከም የዋጋ ግሽበትን ከማባባስ ውጪ ያመጣው ፋይዳ የለም፣ የጠቀመውም ምርታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለሚልኩና አገሪቱ ውስጥ የሚመረቱ የግብርና ዕቃዎችን ለሚገዙ አገሮች ነው፡፡››

የዋጋ ግሽበት – ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ = ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ — ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡ የዋጋ ግሽበት በ2018 (13.83%), በ2019 (15.84%), በ2020 (22.6%) በ2021 (20.6%)

 • በ2010 እኤአ የዋጋ ግሽበት83 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 8.83 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 8.83 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • በ2011እኤአ የዋጋ ግሽበት84 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 7 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 8.84 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 8.84 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • በ2012እኤአ የዋጋ ግሽበት6 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 7 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 15.6 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 15.6  ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • በ2013እኤአ የዋጋ ግሽበት6 የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 7 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 13.6 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ባንክ ያሰቀመጠ ደንበኛ 13.6 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡
 • ‹‹የጦርነት ኢኮኖሚ በ2013ዓ/ም መከሰቱ፣ በተለይም በትግራይ ክልል ያለው ግጭት የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ሳይባብሰው እንዳልቀረ የተጠቆመ ሲሆን፣ በተለይም ከዚህ ቀደም ምርቶችን ለማስገባት ይውል የነበረ የውጭ ምንዛሪ ለመከላከያና ለደኅንነት የሚውልበት ዕድል ሰፊ መሆኑ ይታመናል፡፡
 • የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፡- የመጀመሪያው ጭማሪ በጥቅምት ወር ላይ የተደረገ ሲሆን፣ ማስተካከያው በአማካይ አሥር በመቶ አካባቢ ነበር። ከዚያም በጥር ወር መሸጫ ላይ ተመሳሳይ የአሥር በመቶ ማስተካከያ ከተደረገ በኋላ፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ እስከ አንድ በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ተደርጓል። የዋጋ ግሽበት ባልተረጋጋበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ጭማሪውን እንዳባባሰው ገልጸዋል።
 • መንግሥት ነዳጅ ከውጭ ለመግዛት የሚያወጣው ወጪ በ5 ቢሊዮን ብር በማደጉ ድጎማውን ለመቀነስ መገደዱን ማስታወቁ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በጥቅሉ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ ያደረገው መንግሥት የሚያደርገውን ድጋፍ ከ100 በመቶ ወደ 75 በመቶ መቀነሱን፣ ከሁለት ወራት በፊት ለሕዝብ ይፋ አድርጎ ነበር። ይህም ተገቢ አይደለም ያሉት ባለሙያው፣ ድጎማውም ሆነ ጭማሪ ቀስ በቀስ ሊደረጉ ይገባ እንደነበር ጠቁመዋል።
 • ‹‹ሌላው አገሪቱን ለዋጋ ግሽበት ያጋለጣት የመንግሥት ውሳኔ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረገው የወለድ መጠን ማስተካከያ እንደሆነ ይወሳል። ›› (3)
 • ለማጠቃለል በኦዴፓ ብልፅግና፣ ያደገው ምርት ሳይሆን፣ የዋጋ ንረት ነው! ህዝብ ከዳቦ ጥያቄ ወደ በህይወት የመኖር ጥያቄ የተሸጋገረው ለዚህ ነው፡፡ መጀመሪያ አውደ ኢኮኖሚው በህግና ሥርዓት መመራት አለበት፡፡ በሃገሪቱ የደህንነትና የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ሳይሆን ዜጎች እንደ ከብት እየታረዱ፣ ሴቶች እየተደፈሩ፣ በሠላም ወጥተው መግባት በማይችሉበትና በፈለጉበት ቦታ መኖርና መሥራት ካልቻሉ የኢኮኖሚ እድገት ብሎ ነገር የለም፡፡ የዜጎች በህይወት የመኖር መብትን ያላስከበረ መንግሥት ህዝብን የማስተዳደር፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት የለውም!!! መጀመሪያ የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይሥፈን!!!

(መታወሻነ ለትምህርት ብልጭታ…..ለዶክተር ታደሰ ብሩ ትሁን)

 

ምንጭ፡-

(1)  Inflation rates in Ethiopia (worlddata.info)

(2) የካቲት 22 ቀን 2009 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

(3) በስድስት ወራት ውስጥ በጣም ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ተመዘገበ/10 March 2021/ሳምሶን ብርሃኔ

Leave a Reply