You are currently viewing በከማሼ ዞን በለው ጅጋንፎይ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሶጌ ከተማ ተነስተው ወደ ወሪንቃ ቀበሌ ሲጓዙ በነበሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ…

በከማሼ ዞን በለው ጅጋንፎይ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሶጌ ከተማ ተነስተው ወደ ወሪንቃ ቀበሌ ሲጓዙ በነበሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ…

በከማሼ ዞን በለው ጅጋንፎይ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሶጌ ከተማ ተነስተው ወደ ወሪንቃ ቀበሌ ሲጓዙ በነበሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በከማሼ ዞን በለው ጅጋንፎይ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሶጌ ከተማ ተነስተው ወደ ወሪንቃ ቀበሌ ሲጓዙ በነበሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ፈፅሟል። ጥቃቱ የተፈፀመው መስከረም 3 ቀን 2014 ሲሆን ይህ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ጥቃትም የቤጉ የመስተዳድር አካላት አሹልከው ለአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ለአጋሩ ለጉህዴን በሚሰጡት መረጃ መሰረት ተፈፅሞ ሊሆን እንፈሚችል ነዋሪዎች ጠቁመዋል። ከሶጌ ከተማ ተነስቶ ወደ ወሪንቃ ቀበሌ ፏፏቴ ሲጓዝ በነበረው ልዩ ኃይል ላይ የተናበበው ጥቃት የተፈፀመው በምስራቅ ወለጋ ዞን ፋሲጋ ወረዳ በተለምዶ ሶስተኛ በሚባል አካባቢ መሆኑ ተሰምቷል። የአሸባሪው ቡድን አባላት ቁጥራቸው ያልታወቁ የልዩ ኃይል አባላትን ከመግደል በተጨማሪ 1 ፓትሮል ስሪ ኤፍ አቃጥለዋል ተብሏል። ከጥቃቱ የተረፉና የቆሰሉ የቤጉ ልዩ ኃይል አባላት መስከረም 3 ቀን 2013 ምሽት ላይ ወሪንቃ መግባታቸውን ከስፍራው ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በስንቅና በትጥቅ የሚደግፈው የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን ሀምሌ 8፣9 እና 10 ቀን 2013 ዓ/ም 53 አማራዎችን መግደሉ፣ ከ70 በላይ አድራሻቸውን ማጥፋቱና ከ7,500 በላይ አማራዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ ይታወሳል። በተጨማሪም ነሃሴ 9 ቀን 2013 የአንድ ዓመት ህጻንን ጨምሮ 12 የአማራ እና 6 የበርታ ተወላጆችን ወሪንቃ ቀበሌ ላይ መግደሉ አይዘነጋም። ባሎቻቸውን፣ ወንድማቸውንና ጎረቤታቸውን ከፊታቸው በአሰቃቂ መልኩ የረሸነው ተላላኪው የጉህዴን ቡድን 7 የወሪንቃና የአካባቢው ሴቶችን አግቶ በመውሰድ በቡድን መድፈሩ፣ከመካከላቸውም 4ቱን ለ4 ቀናት ጫካ ውስጥ በቡድን ሲደፍር መሰንበቱና መጨረሻ ላይ ማምለጣቸው ተገልጧል። ይሁን እንጅ በሚያሳዝን ሁኔታ በቡድን ከተደፈሩት መካከል በነቀምት ሆስፒታል ስትረዳ የቆየችው አንደኛዋ እህታችን ነሃሴ 16 ቀን 2013 ህይወቷ ማለፉ ከነዋሪዎቹ ተረጋግጧል። በተመሳሳይ በድባጤ ወረዳ ግልገል በለስ መውጫ አካባቢ መስከረም 3 ቀን 2014 ተኩስ የከፈተው የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን በቡድኑ በኩል የተገደለውን ለማወቅ ባይቻልም ከወገን ጦር አንድ መግደሉና አምስት ማቁሰሉ ተሰምቷል። መስከረም 4 ቀን 2014 በተመሳሳይ በድባጤ ወረዳ 02 ቀበሌ ላይ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ተኩስ ከፍቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply