በከተማችን አዲስ አበባ 51 ህገ-ወጥ እርድ ተይዞ በግብረ-ሃይሉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ፡፡ በአራት ክፍለ ከተሞች በተለዩ ቦታዎች በተደረገ አሰሳ 51 ህገ-ወጥ እርድ ሲያከናኑ መያዛ…

በከተማችን አዲስ አበባ 51 ህገ-ወጥ እርድ ተይዞ በግብረ-ሃይሉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ፡፡

በአራት ክፍለ ከተሞች በተለዩ ቦታዎች በተደረገ አሰሳ 51 ህገ-ወጥ እርድ ሲያከናኑ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታዉቋል፡፡

በከተማ ደረጃ ገበያን ለማረጋጋት ከሳምንታት በፊት የተቋቋመው ግብረ-ሀይል በአራት ክፍለ ከተሞች ማለትም ቦሌ፤ ንፍስ ስልክ ላፍቶ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ህገ-ወጥ እርድ የሚከናወንባቸው ቦታዎችን ለይቶ ባደረገው ክትትል መሰረት በዛሬው እለት 51 በህገወጥ መንገድ እርድ ሲያከናን እጅ ከፍንጅ በመያዝ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በእነዚህ አካባቢዎች 229 በግና ፍየሉች በህገ-ወጥ መንገድ ሊታረዱ ሲሉ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሚዬሶ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply